በጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ መጽሐፍትን በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተያዙ ነጋዴዎች ተቀጡ፡፡

ወ/ሮ የምሥራች ማሞ በአርባ ምንጭ ከተማ የነጭ ሣር ቀበሌ ንግድ እና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ እንዳሉት ከ50 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው 310 የተለያዩ መጽሐፍቶች በህገ ወጥ መንገድ ከተሰማሩ የመጽሐፍት አዟሪዎች በነጭ ሣር ቀበሌ ህገ ወጥ ግብረ ኃይል አማካኝነት ሊያዝ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

የመጽሐፍትን ዋጋ በማናርና የንባብ ባህል በዚህ ምክንያት እንዲዳከም ከማድረጉም በላይ በእነዚህ ህገ ወጥ አዟሪዎች በመጀመሪያ ዙር ማስተማሪያ የቃል ማስጠንቀቂያ ፣ሁለተኛ ዙር በእያንዳንዱ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ በነፍስ ወከፍ አንዳንድ ሺህ ብር ቅጣት ቢጣልባቸውም ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው በ3ኛ ዙር በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበረውን ልዩ ልዩ መጽሐፍት በመውረስ ለመንግስሥት ገቢ ማድረግ ተችሏል፡፡

አቶ ሸዋን ግዛው ኡርጌ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ም/ኃላፊ የወጣቱ የንባብ ባሕል እንዲጎለብት መጽሐፍት በብዛትና በፍትሃዊ ዋጋ መቅረብ እንዳለባቸው ጠቅሰዋል፡፡

በአርባ ምንጭ ከተማ በቁጥር 4 ማዕከል መኖሩን አስታውሰው ባሉት ቤተ መጽሐፍት  የመጽሐፍት እጥረት እናዳለ እና የሚደረገላቸው ድጋፍ በመጠኑም ቢሆን ይህን ችግር እንደሚቀርፍላቸው እና አንባቢ ትውልድም ለመፍጠር ህገ ወጥ አዟሪዎችን መቆጣጠር እንደሚገባ መግለፁን ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።