እንያት ሆስፒታል በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ታካሚዎችን ተደራሽ በማድረግ ዘመናዊ ህክምና በዎላይታ ሶዶ ከተማ እየሰጠ መሆኑ ተገለፀ።
ከቅርብ ወር በፊት በዎላይታ ሶዶ ከተማ ራሱ ባስገነባው ግዙፍ ህንፃ ስራውን በይፋ የጀመረው እንያት ሆስፒታል ከፍተኛ ልምድና ዕዉቀት ያላቸዉን ባለሙያዎች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና ከቅዱስ ጳዉሎስ ሚሌኒየም ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማስመጣት የላቀና ዘመናዊ አገልግሎትን መስጠት በጀመረ ጥቂት ቀናት ውስጥ ብቻ ከከተማው፣ ከዞኑ እንዲሁም አጎራባች አካባቢዎች በርካታ ቁጥር ያላቸዉን ተገልጋዮችን በተቀላጠፈ ሁኔታ እያስተናገደ በመሆኑ ሆስፒታሉ ከፍተኛ ደስታ ይገልጻል።
ከላይ ከተጠቀሱት ባለሙያዎች በተጨማሪ እጅግ ዘመናዊ መሳሪያዎችን በማካተት በተደራጀዉ ላቦራቶሪያችንና አልትራሳዉንድ በተጨማሪም የልብ ምርመራ ኢኮካርድዮግራፊ በምቹ ቦታ በከተማዋ ከሚገኙ በርካታ የግልና የመንግስት እንዲሁም ክርስትያን ሆስፒታልን ጨምሮ እየተላኩ የሚገኙትን ምርመራዎችንና ታካሚዎችንም ተቀብሎ በቅልጥፍና በምቹ ህክምና ማዕከል በማስተናገድ ላይ እንደሚገኝም ከሆስፒታሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል🙏
ሆስፒታሉ ከስልሳ ሚሊዮን ብር በላይ ባስገነባው በራሱ ግዙፍ ህንፃ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት ኮንሰልታንት ራዲዮሎጅስቶችን በመያዝ ቀዳሚና ተመራጭ ሆስፒታል የሚያደርጉትን አገልግሎቶች ይዞ ቀርቧል።
ለአብነትም የውስጥ ደዌ፣ የቀዶ ጥገና፣ የህጻናት ህክምና፣ የማህጸንና ፅንስ እንዲሁም የስነ ደዌ ህክምና የሚሰጡ በርካታ ስፔሻሊስቶች ይዞ እየሰራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
የአልትራሳውንድ፣ የኢኮካርድዮግራፊ፣ የራጅና የሲቲ ስካን አገልግሎት በስፔሻሊስቶች ከሚሰጡ ህክምናዎች በጥቂቱ ሲሆን የመለስተኛ ቀዶ ህክምናም በተደራጀ መልኩ ለታካሚዎች እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል።
ሆስፒታሉ በመጀመሪያዉ ዙር አስራ ሰባት (17) የሚሆኑ በተለያየ የህክምና ሙያ ዘርፍ ስፔሻላይዝ ያደረጉ ባለሙያዎችንና አምስት (5) ጠቅላላ ሐኪሞችን በመያዝ የህክምና አገልግሎትን በሰፊው እየሰጠ ይገኛል!!
እነዚህም👇
👉የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት/ INTERNISTS (ሁለት)
👉የቀዶ ጥገና ህክምና ስፔሻሊስት/ SURGEONS (ሁለት)
👉የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት/ PEDIATRICIANS (ሁለት)
👉የማህጸንና ፅንስ ህክምና ስፔሻሊስት/ OBSTETRICIAN AND GYNECOLOGISTS (ሁለት)
👉የስነ ደዌ ስፔሻሊስት/ PATHOLOGISTS (ሁለት)
👉የአልትራሳውንድ፣ የኢኮካርድዮግራፊ፣ የራጅና የሲቲ ስካን ስፔሻሊስት / RADIOLOGIST (ሁለት)
👉የሽንት ፊኛና የሽንት ቱቦዎች ስፔሻሊስት/ UROLOGIST (አንድ)
የካንሰር ህክምና ስፔሻሊስት/ONCOLOGIST (አንድ)
👉ከአንገት በላይ ህክምና ስፔሻሊስት/ ENT SURGEON (አንድ)
👉የአጥንትና የመገጣጠሚያ ህክምና ስፔሻሊስት/ ORTHOPEDICIAN (አንድ)
👉የቆዳና የአባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስትDERMATOVENEROLOGIST (አንድ)
👉ጠቅላላ ሀኪም / GENERAL PRACTITIONER (አምስት)
ከተለያዩ ጤና ተቋናት የሚላኩ ምርመራዎችን ሆስፒታሉ መስራት መጀመሩ የተገለፀ ሲሆን ከየትኛዉም የህክምና ተቋማት በመምጣት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻልም ተነግሯል።
እንያት ሆስፒታል🙏
አድራሻ ⏩ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ከብሩህ ተስፋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፊትለፊት ያገኛሉ⏬ ስልክ ቁጥር ⏬
0465512916
0913469148
እንያት የዘመናዊ ህክምና ማዕከል🙏
