በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ኮምፕርሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሀገር አቀፍ የሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት 4ኛ ዙር መረጃን መሠረት ያደረገ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።
ሀገር አቀፍ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት 4ኛ ዙር (መረጃን መሠረት ያደረገ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ) ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ከደቡብ ክልልና ከዎላይታ ዞን ጤና ቢሮ የመጡ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ኮምፕርሰሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሰርቭስ ዳይሬክተሮች ተሳትፈዋል።
በምክትል ፕረዚዳንት ማዕረግ የጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር ሉቃስ ዲንጋቶ ለተሳታፊዎች በጤና ተቋም ላይ እንደመስራታችንና የጤና ባለሙያዎች እንደመሆናችን መጠን ፤ በጥምረት ለህብረተሰባችን የተሻለ የጤና አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ታሪክ ሰርተን ሊናልፍ ይገባል ብለዋል።
ሀገር አቀፍ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ከ2004 ዓ.ም.ጀምሮ ለአሥር ዓመታት የሕክምና አገልግሎት ጥራት በጥምረት ለማሳካት በሀገራችን እየተካሄደ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሶ፤ መሪ ሆስፒታሎች ለአባል ሆስፒታሎች በቴክኒክ ፣በግብዓት እንዲሁም በአቅም ግንባታ እየተደጋገፉ በጥምረት የተሻለ የጤና አገልግሎት ለህዝባችን ተደራሽ ለማድረግ የታሰበ ኘሮግራም መሆኑን አቶ ቢኒያም ሽፈራው የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ሜዲካል ሰርቭስ ዳይሬክተር ገልጸዋል።
አቶ ቢኒያም አክለው፥ ሀገር አቀፍ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት አራተኛ ዙር (EHAQ 4th Cycle ) መረጃን መሠረት ያደረገ የሕክምና አገልግሎት በትኩረት አቅጣጫዎች ማለትም ተመላላሽ ሕክምና አገልግሎት፣ ጨቅላ ህፃናት ጥብቅ ጥንቃቄ አገልግሎት ፣ የድንገተኛ እና የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለማሻሻል የታሰበ መሆኑን በማብራራት ሠፊ ገለፃ አድርገዋል።
የዩኒቨርስቲው ኮምፕርሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሕክምና ጥራት ማሻሻያና ማጎልበቻ ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ጎአ ሀገር አቀፍ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ባለፉት ሦስት ዙሮች መሪው የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስት ኮምፕርሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአባል ሆስፒታሎች በጋር የተሰሩ ሠፊ ሥራዎችን ገለፃ አድርጓል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በጥምረት የተሻለ የጤና አገልግሎት ለማሳካት ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችንና ቀጣይ አቅጣጫ በማጥራት መሪው እና አባል ሆስፒታሎች መግባቢያ ሠነድ በመፈራረም ፕሮግራሙ ተጠናቋል ሲል የኮሌጁ ኮ/ሕ/ግንኙነት ዘግቧል።
ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ከደቡብ ክልልና ከዎላይታ ዞን ጤና ቢሮ የመጡ ኃላፊዎች ፣ በምክትል ፕረዚዳንት ማዕረግ የጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር ሉቃስ ዲንጋቶ ፣ አቶ እሸቱ አየለ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ ዶክተር መንግሥቱ መስቀሌ ቺፍ አካ/ጉዳዮች ዳይሬክተር ፣አባል ሆስፒታል ሥራ አሰኪያጆች ና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ኮምፕርሰሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሰርቭስ ዳይሬክተሮች ተሳትፈዋል ።
