በዎላይታ ሶዶ ከሌዊ ሪዞርት ሆቴል እስከ ግብርና ኮሌጅ በ2013 ዓ ም ለማሰራት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የአለምአቀፍ ጨረታ ያወጣ ቢሆንም እስካሁን ምንም እንቅስቃሴ አለመጀመሩ በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ እየፈጠረ ነው ተባለ።

በሶዶ ከተማ ከሌዊ ሪዞርት አንስቶ ግብርና ኮሌጅ መንገድ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከማሳለጥ አኳያ በአገልግሎት ጥራትና ስፋት ውስንነት የሚስተዋልበት ዋናው የአስፋልት መንገድ ደረጃውን በጠበቀ በኮንክሪት አሰፋልት ለማስራት ጨረታ ወጥቶ ነበር።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በዎላይታ ሶዶ ከተማ ባለፉት ዓመታት በከተማው ዕድገትና ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ እንቅስቃሴ ምክንያት በማድረግ ለትራፊክ አደገኛ መሰል የትራንስፖርት አገልግሎት ውስንነትና ችግሮች ሲስተዋልበት የነበረውን ከሌዊ ሪዞረት አንሰቶ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ የሚወስደውን ዋና የአስፋልት መንገድ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በ2013 በጀት ዓመት የአስፋልት ኮንክሪት ለመስራት አለም አቀፉ ጨረታ እንደወጣ በመረጃ አስደግፈን ማሳወቃችንም ይታወቃል።

በተጨማሪም ከሶዶ አውራጎዳና ቆንቶ አረካ አስራ አምስት ክ.ሜ መንገድ በአጠቃላይ እንደሚሰራ ጨረታ ማውጣቱም የሚታወስ ነው።

ነገር ግን እስካሁን ስራውን ለመጀመር የሚደረግ እንቅስቃሴ አለመታየቱ ለብዙዎች ቅሬታ መፍጠሩን በመግለፅ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላትን ማብራሪያ እንዲሰጡበት ጠይቆናል።

የመንገዱ ግንባታ የዘገየበት ዝርዝር መረጃና ምክንያት ከሚመለከታቸው አካላት እንዳገኘን እንደሚናደርስ ከወዲሁ እንገልፃለን።