
በዎላይታ ሶዶ ከሌዊ ሪዞርት ሆቴል እስከ ግብርና ኮሌጅ በ2013 ዓ ም ለማሰራት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የአለምአቀፍ ጨረታ ያወጣ ቢሆንም እስካሁን ምንም እንቅስቃሴ አለመጀመሩ በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ እየፈጠረ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።
የህዝብ ቅሬታ መነሻ አድርጎ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ኃላፊ የሆኑትን አቶ ሳምሶን ወንድሙን በጉዳዩ ዙሪያ በስልክ አነጋግሮ ምላሽ አግኝቷል።
አቶ ሳምሳን በጉዳዩ ዙሪያ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ምላሽ ሲሰጡ “በ2013 ዓ.ም የመንገዱን ግንባታ ባለስልጣኑ መጀመር ያልቻለው በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት ነበር” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

በከተማዋ ዕድገት ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ እንቅስቃሴ ምክንያት ለትራፊክ አደገና መሰል የትራንስፖርት አገልግሎት ውስንነትና ችግሮች እየተስተዋለ የሚገኘው ከሌዊ ሪዞረት አንሰቶ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ የሚወስደውን ዋና የአስፋልት መንገድ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በ2013 በጀት ዓመት የአስፋልት ኮንክሪት ለመስራት አለም አቀፉ ጨረታ በህጋዊ ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ማሰራት አለመቻሉን ይናገሩ እንጂ መቼ እንደሚሰራ ኃላፊው አልገለፁም።
ወደፊት በመንገዱ ግንባታ ዙሪያ መቼ እንደሚጀመር ባለስልጣኑ መረጃ እንደሚሰጥ የባለሥልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ኃላፊው አክለው ተናግረዋል።