ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአስተዳደር ጉባኤው ሹመት ሲያበስር በደስታ ነው ሲል በመግለፅ ይጀመራል።
የክራይስስ ግሩፕ ፕረዚዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ሮበርት ማሌይ ክራይሲስ ግሩፕ የተለያዩ ባህልና ወግ ያላቸው ሀገራትን የመሩ መሪዎች ልምድና እውቀታቸውን በእጅጉ እንደሚጠቁሙት ተናግረዋል።
“የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም የድርጀቱ አላማ ለማሳካት ወሳኝ ክህሎትና ልምድ ያካበቱ በመሆኑ ስራችንን ያጎላሉ፣ በአለም ላይ አስቸጋሪ ግጭቶችን ለመከላከል እና ለመፍታት በምንፈልግበት ጊዜ ከእነሱ ጋር በቅርበት ለመስራት እጠባበቃለሁ” ሲሉም ፕሬዝዳንቱ እምነታቸውን በተመረጡበት ወቅት አስረድተዋል።
“የአቶ ኃይለማርያም ጥምር ልምድ፣ ጥበብ እና ተፅእኖ የክራይሲስ ግሩፕ በተለዋዋጭ ጂኦፖለቲካዊ እና አካባቢያዊ እውነታዎች ላይ መጓዙን እንዲቀጥል እና በግጭት አፈታት ላይ ያለው ድምጽ በአስፈላጊ ቦታዎች እንዲሰማ ያግዛል” ስሉም ፕረዚዳንቱ የአለምአቀፉን ድርጅትን በቦርድ አባልነት የተቀላቀሉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ገልፀዋል።
ኢንተርናሽናል ክራይሲስ ግሩፕ ጦርነቶችን ለመከላከል እና የበለጠ ሰላማዊ ዓለምን የሚገነቡ ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ የሚሰራ ራሱን የቻለ አለምአቀፍ ድርጅት ሲሆን ግጭትን ለመከላከል ማንቂያውን በማሰማት ማህበረሰቡ ለመልካም አስተዳደር እና ሁሉን አቀፍ ፖለቲካ ድጋፍ እንዲያገኝ ከተለያዩ የግጭት ተዋናዮች ጋር በቀጥታ እንገናኛለን መረጃ ለመፈለግ እና ለመለዋወጥ እንዲሁም ለግጭቶች ሰላማዊ መፍትሔ የሚያፈላልግ በአለምአቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሀገር መሪነት ያገለገሉና ታዋቂ ግለሰቦች ያሉበት የተደራጀ አለምአቀፍ ድርጅት መሆኑን ከድርጅቱ ድረገጽ የዎላይታ ታይምስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ከዩኒቨርስቲ አመራርነት ጀምረው በተለያዩ ደረጃ አመራርነት የመሩ፣ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉና በአፍሪካ ሆነ በአለም አዲስ ክስተት በራሳቸው ፈቃድ ስልጣንን በሰላማዊ መንገድ በማስተላለፍ ሳያርፉ በሀገሪቱ ሆነ በአለምአቀፍ መድረክ ባካበቱት ጥልቅ እውቀትና ልምድ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ።

