fb_img_16477521828175810079740040825346

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከሩሲያ ጋር ውጤት የሚያስገኝ የሰላም ንግግር በአስቸኳይ ማድረግ እንደሚፈልጉ አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ ለሕዝባቸው ባስተላለፉት በቪድዮ የተቀረጸ መልዕክት ላይ እንዳሉት በግዛታቸው ውስጥ ግዙፍ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች ካለችው ሩሲያ ጋር “ካለምንም መዘግየት ትርጉም ያለው” የሰላምና የደኅንት ንግግር እንዲጀመር ጠይቀዋል።

ይህም ሩሲያ በአገራቸው ላይ በከፈተችው ወረራ በፈጸመችው “ስህተት” የሚደርስባትን ጉዳት ለመቀነስ ያላት ብቸኛው እድል ነው ሲሉ ዜሌንስኪ ተናግረዋል።

“ለመገናኘት፣ ለመነጋገርና የዩክሬንን የግዛት አንድነት እንዲሁም ፍትህን ወደነበረበት ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ዜሌነስኪ ለሩሲያ ጥሪ አቅርበዋል።

“ይህ ካልሆነ ግን ሩሲያ ከሚገጥማት ውድቀት ለመውጣት በርካታ ትውልዶችን መጠበቅ ሊያስፈልጋት ይችላል” ብለዋል። BBC