GHGFJCGFH

በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር ምሽቱ 4:35 ላይ በሴቶች ምድብ የተደረገው የ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት ድል ተቀዳጅተዋል።በውድድሩ ጉዳፍ ፀጋይ አንደኛ፣ አክሱማዊት አምባዬ እና ሒሩት መሸሻ ሁለተኛና ሶስተኛ በመውጣት የብር እና የነሀስ ሜዳልያ ማስገኘታቸውን ከኢፕድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።