
“በኢትዮጵያ እየለማ ያለው የቆላ የበጋ መስኖ ስንዴ ከውጭ የሚገባውን ሙሉ ለሙሉ ለመተካት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ላይ ነው”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
በኢትዮጵያ እየለማ ያለው የቆላ የበጋ መስኖ ስንዴ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ ሙሉ ለሙሉ ለመተካት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዓለም ባንክ ከአፍሪካ ቡድን 1 ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታውፊላ ኒያማድዛብ እና በኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ከሆኑት ኦስማን ዲዮን ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ የኩታ ገጠም ስንዴ ምርታማነትን ጎብኝተዋል።
