1648017360687

በዎላይታ ሶዶ ከተማ የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት ውይይት መድረክ ተጀመረ

በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚና የኢፌዴሪ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጨምረው የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ፣ ሌሎች አመራሮችና ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ህብረተሰብ ተገኝተዋል፡፡

ውይይት መድረኩ ሕዝቡ የሚያነሳቸውን ወቅታዊ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ከጉባኤው አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውንና በየደረጃው ያሉ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የጋራ መግባባት ለመድረስ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በዞኑ በሶስቱ ሪፎርም ከተማዎችና በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ማዘጋጃ ቤት ከተማዎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ህዝቡ ውይይት መጀመሩን ከየስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
wolaitatimes.com