
በጋሞ ዞን በምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፍ/ቤት በልጁ ላይ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል በፈፀመ ወላጅ አባት ላይ የእስር ፍርድ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

በደቡብ ክልል በምዕራብ ዓባያ ወረዳ ብርብር ከተማ መንደር ሰባት ነዋሪ የሆኑት ኢንስፐክተር ግርማ ጌታቸው የገዛ ልጇን ዕድሜዋ 20 ዓመት የደረሰና የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን መንግሥት ባስታጠቀው ሽጉጥ በማስፈራራት በቀን 6/6/2014 ዓ/ም ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ በጉልበት የግብረ ስጋ ግንኙነት ሲፈፅም ልጅቷ በመጮኃ ጎረቤት በመሰማት መደፈሩዋን ከአንደበቷ ሰምተው ሲያረጋግጡ ለፖሊስ ጥቆማ በማድረግ የማጣራት ስራ በመስራት በህግ ሲታይ ቆይቶ ጋሞ ዞን የምዕራብ አባያ ወረዳ ፍ/ቤት በተከሳሹ ላይ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት 9 ዓመት ከ3 ወር ፅኑ እስራት ፍርድ መተላለፉን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዘግቧል፡፡
