16480396507734412244464067376277

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ በብላቴ ወንዝ በተለምዶ ፏፏቴ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ 7 ሰዎች ወንዙን አቋርጠው በማለፍ ላይ ሳሉ ሃይለኛ ደራሽ ውሃ መልቶ ይዟቸው መሄዱ ተገልጿል።

በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 4 ሰዓት አከባቢ በቁሊቶ ከተማ ገበያ ውለው በሰላም ወደቤታቸው እየሄዱ ሳሉ ነው ድንገተኛ አደጋው የተከሰተው።

በደራሽ ውሃ የተወሰደውን ሰው ለማስተረፍ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ርብርብ ብያድርግም ደራሽ ውሃው ሃይለኛ በመሆኑ አንድም ሰው ለማትረፍ አልተቻለም። የሟቾቹ አስክሬንም አልተገኘም ። የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ለሟች ቤተሰቦቹ መፅናናትን መመኘቱን ከከተማ አስተዳዳር የተላከልን መረጃ ያመለክታል።