ሕዝብን የሚያማርሩና በተለይም በሌብነትና ብልሹ አሠራሮች እጃቸው አለባቸው ተብለው በግምገማ ከኃላፊነታቸው የተነሱ አመራሮች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስታወቋል፡፡

የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊና የማዕከላዊ ኮሚት አባል የሆኑት አቶ አብራሃም ማርሻሎ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በከተማም ሆነ በገጠር እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ ሕዝብን በሚያማርሩ ጉዳዮች ዙሪያ ሕዝቡም ሆነ የፓርቲው አባላት ውይይት አካሂደዋል፡፡

በዚህም ሕዝብ በተደጋጋሚ ያነሳቸው እንዲስተካከሉለት ከጠየቃቸው ጉዳዮች ውስጥ ሌብነት፣ ሥራ አጥነት፣ አድሎአዊ አሠራር፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ አልቀው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውሉ አለማድረግ፣ የአመራሩ የሥነ ምግባር ችግሮችና የመሳሰሉት ጉዳዮች መሆቸውን አንስተዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: