በብላቴ ማእከል በ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለሚገነባ አውሮፕላን ማረፊያ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

በብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማእከል ለሚገነባው አውሮፕላን ማረፊያ የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡት የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የኢፌድሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ቩም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላና የደቡብ ክልል ርእስ መስተዳደር ርስቱ ይርዳው ናቸው።

የአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ የሶዶ መገንጠያ ድምቱ(ብላቴ) የ75 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድን ያካተተ ነው።

ከመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ስነ ስርአቱ ጎን ለጎን የልዩ ዘመቻዎች ሀይልና የሪፐብሊካን ጥበቃ ሀይል በአል ስነ ስርአት እየተካሄደ ነው።

በበአሉ ለኮማንዶ፣ አየር ወለድ ልዩ ሀይል፣ ጸረ ሽብርና ባህር ጠለቅ ክፍሎች የሜዳይ ሽልማት እንደሚሰጥ የወጣው መርሀ ግብር አመላክቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *