

በደራሲ ማንያህልሻል ማዴቦ የተጻፈዉ ታኒ ዎላይታ የተሰኘ በጉድፈቻ ህፃናት ላይ ትኩረቱን ያደረገ መፃፍ የኦንላይን መገበያያ በሆነዉ አማዞን ላይ ለሽያጭ በቅቷል።
ማንያህልሻል ማዴቦ ተወልዳ ያደገችው በዎላይታ ሶዶ ከተማ ሲሆን ከኢትዮጵያ እ ኢ አ በ2013 ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አሜርካ ተዛወረች፣ አሁን በሰሜን ቨርጂኒያ ከባለቤቷ እና 3 ልጆቿ ጋር የምትኖረዉ ማንያህልሻል በጉዲፈቻ ለሚያድጉ ህጻናት የቤተሰብ ፍለጋ፣ የቋንቋ ሥልጠና፣ የባህል ዝንባሌ፣ የደብዳቤ ትርጉም፣ የስልክ ጥሪ እና ትርጓሜ በፈቃደኝነት እየሰራች ነው።

27 የማደጎ ልጆችን ከወላድ ወላጆቻቸው ጋር እንደገና አገናኝታለች። ዎላይታ ውስጥ ተወልዳ ያደገች ሴት እንደመሆኗ መጠን ስለ ዎላይታ ባህል እና ወግ ብዙ መረጃ አላት። ከበርካታ የማደጎ ህጻናትን ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር ለማገናኘት ብርካታ የሰራችዉ የማደጎ ህጻናት መብት ተሟጋች ደራሲ ማንያሂሊሻል ማደቦ ቤተሰቦች እና ልጆች ስለትውልድ ቦታቸው የሚጠይቋቸውን ብዙ የተለመዱ ጥያቄዎችን በመጻፉ ለመመለስ ሞክራለች።
እኔ ዎላይታ ነኝ የተሰኘዉ መጸሐፍ የመጀመሪያዋ መጽሃፍ ነው ሁሉንም ጥያቄዎች ላይመልስ ይችላል ነገር ግን በተቻለ መጠን ብዙ መረጃዎችን አካትቷል ስትል ደራስዋ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተናግራለች።
i would like to say congratulation! Hashu hagawu tages
Good
Nice
Kehi daro lo”o.