muctar

አትሌት ሙክታር ኢድሪስ በስፔን የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ የቦታውን ሪከርድ በመስበር ጭምር አሸንፏል፡፡

አትሌቱ 28:34 በሆነ ጊዜ በመግባት ነው የቦታውን ሪከርድ ጭምር በማሻሻል መሸነፍ የቻለው፡፡

በተመሳሳይ በቱርክ ኢስታንቡል በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ፀሐይ ገመቹ 1:05:52 በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ በዚሁ መርሃ ግብር አትሌት በቀለች ጉደታ 1:06:35 በሆነ ሰዓት በመግባት ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ውድድሩን ማጠናቀቋን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡