wtn

የልማት ማህበሩ 21ኛ አመት ጠቅላላ ጉባኤ በጉታራ አዳራሽ በተካሄደዉ ጉባኤ ከወረዳ እስከ ፌዴራል ደረጃ የሚገኙ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ዉይይቱ ተካሂዷል፡፡

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዎላይታ ዞን ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ ሲሆኑ ልማት ማህበሩ ባለፉት 21 አመታት ዉስጥ ያስመዘገባቸዉ ድሎች በህዝቡ ሁለንተናዊ ማንነት ዉስጥ ሰርጸዉ እንዲቆዩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገም ጭምር ነዉ በንግግራቸዉ የገለጹት፡፡ የዎላይታ ልማት ማህበር ታታሪውንና ሥራ ወዳዱን የወላይታ ህዝብ በማስተባበር የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ እየሰራ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ማህበሩ በሰው ሀብት ልማት፣ በዘላቂ ኑሮ ማሻሻያና በተቀናጀ ጤና ዘርፎች ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ለህብተሰቡ ተደራሽ በማድረግ በተለያዩ ስራዎችና በዞኑ በሚገኙ በተለያዩ ወረዳዎች በምግብ እጥረት የተጎዱ ተጋላጭ ህጻናትን እየረዳ መቆቱንም ገልጸዋል።

የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትና የማህበሩ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ በበኩላቸው ለጉባኤ ተሳታፊዎች እንኳን በደህና መጣችሁ መልዕክት እና የልማት ማህበሩን ተግባራት እንዲሁም የሊቃ ትምህርት ቤት ዉጤት የሁሉም ወላይታ ህዝብ ልፋት ዉጤት እንደሆነም ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

በጉባኤው የ2013 ዓ.ም ዕቅድ ክንውን፣ የበጀትና ቁጥጥር ኮሚቴ እና ኦዲት ሪፖርቶች ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡

ማህበሩ ባለፉት ጊዜያት ከዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተዉጣጡ የጥናት ቡድኖች በበጎ ተዕጽኖ ጥናት ውጤት ቀርቦ በቀጣይም ስራዎችን በጋራ ለመስራት ቃል ገብተዋል፡፡

 በመጨረሻም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ተቋማትና ግለሰቦች የማበረታቻ ሽልማትና ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

https://www.facebook.com/wolaitatime