FB_IMG_1648565249571

የደቡብ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ የድንጋይ ከሰል (Coal site) ጉብኝት በዛሬው ዕለት ተደርጓል።

የደቡብ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በሆኑት በወ/ሮ አጸደ አይዛ የተመሩ የኤጀንሲው አመራር ፣ ከፍተኛ የዘርፉ ባለሙያዎች ፣ የዞንና የቀበሌ አመራሮች በዎላይታ ዞን በኪንዶ ዲዳዬ ሼላ መቀራ ቀበሌ ላይ የድንጋይ ከሰል ኮል ሳይት ጉብኝት አድርገዋል።

በሀገራችን በከፍተኛ ሁኔታ እየተስተዋለ የሚገኘውን የሲሚንቶ ችግር ለመቅረፍ መንግስት እንደመፍትሄ ከያዘው አቅጣጫ በየአካባቢው ያሉ የተፈጥሮ ማዕድናትን በመለየት ወደ ሥራ እንዲገባ ማድረግ መሆኑን የገለፁት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አጸደ አይዛ ናቸው።

በተጨማሪም ባለሀብቶች የቅኝትና የምርመራ ፍቃድ ያገኙበት ቦታ በመገኘት ከቀበሌው አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጎ ከፍተኛ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራም ተሠርቷል።

ለወላይታ ሥልጣኔ መነሻ የሆነው ከሰል ድንጋይ ዛሬ ላይ በለውጡ አመራር ትኩረት ተሰቶ እየተሰራ ይገኛል።

ከሰል ድንጋይ/ከቅሪት አካል የሚገኝ ነዳጅ/ኃይል Carbon with H,S,O &N

ከጥቁር እስከ ቡናማ ጥቁር ቀለም ይዘው ዝቅጤ አለት ውስጥ የሚፈጠር  ለብዙ ዓመታት የተከማቸ የዕፅዋት ቅሪት ነው፡፡ ይህ ማዕድን በአብዛኛው ካርበን ይዘት ሲኖረው ሃይድሮጅን፣ ሰለፈር፣ ኦክስጅንና ናይትሮጅን በከፊል ይዘው ይፈጠራሉ፣

የተለያየ ዓይነት የከሰል ድንጋዮች ሲኖሩ እነርሱም፡-

ሊግናይት፡- ቡናማ ቀለም ይዘት ያለውና ዝቅተኛ የካርበን ክምችት በመኖሩ ኃይል የማመንጨት አቅሙ አነስተኛ ነው፣ ለኤሬትሪክ ኃይል ማመንጫነት አገልግሎት ይውላል፣

ሳብ-ቢቱሚነስ፡- ቡናማ ጥቁር ቀለም ያለውና አብረቅራቂ ያልሆነ/ደብዘዝ ያለ ከሊግናይት የተሻለ አቅም ያመነጫል፣ ለኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫነት አገልግሎትና ለኬሚካል ውህድ አገልግሎት፣

ቢቱሚነስ፡- ጥቁር ቀለምና በተወሰነ ደረጃ ቡናማ ቀለም ይዘትና መካከለኛ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን አብለቅላቂና ለስላሳ የሚመስል ይዘት ያለውና በጉልህ የማይታይ አብረቅራቂና ፈዛዛ ንብርብሮሽ በከሰሉ ላይ ይታያል፣ ለኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫነት አገልግሎት፣ ብረት ማቅለጫነትና ለኢንዱስትሪ ሃይል ሰጭነት ያገለግላል።

የድንጋይ ከሰል ኢንዱስትሪ ጠንካራ እና ቡናማ የድንጋይ ከሰል በማምረት እና የመጀመሪያ ደረጃ ማቀነባበሪያ (ማበልጸጊያ) ላይ የተሰማራ ሲሆን በሠራተኞች ብዛት እና በምርት ቋሚ ንብረቶች ዋጋ ትልቁ ኢንዱስትሪ ነው።

የድንጋይ ከሰል በኢንዱስትሪ ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ ከሚውሉ ጠቃሚ ሀብቶች አንዱ ነው። በዚህም መሠረት በዓለም ላይ በተለያዩ ቀጠናዎች የሚፈጠሩ ጦርነቶች የዓለም ገበያ ከፍና ዝቅ እንድል ሚናቸው ሰፍ ነው።

ይህን ተከትሎ በአገራት የሚፈጠረውን የዋጋ ንረት ለመከላከል የራስን ዓቅም ማጎልበት ቀዳሚ ጉዳይ ልሆን ይገባል እያልን ዛሬ ላይ ትኩረት እየተሰጣቸው የሚገኘው የድንጋይ ከሰልን በማምረት እንዱስትሪዎች ውስጥ በሃይል መቆራረጥ የሚፈጠረውን ክፍተት በመሸፈን እና ከነዳጅ ጥገኝነት በማላቀቅ ያሉን ውስን እንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው እንድያመርቱ በማድረግ ያሉንን የተፈጥሮ ፀጋዎቻችንን ወደ ተግባር በማስገባት የኢትዮጵያን ልዕልና እናረጋግጣለን።