
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ በኩል የክላስተር አደረጃጀትን አስመልክቶ የተሰጠው መግለጫ ፍትሃዊነቱ የጎደለ ነው ሲሉ የኮንታ ዞን ነዋሪዎች ገለፁ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ም/ል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ከኢቲቪ 4ማዕዘን ጋር በነበራቸው ቆይታ 4 ማዕከላት የሚኖሩትን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተሞችን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ የኮንታ ዞን ህዝቦች ፍትሃዊነቱ የጎደለ ክፍፍል ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል።

ኮንታ እንደ ዞን ለሀገር የሚበቃ ኢኮኖሚ ያላት፣ እንደሀገር በርካታ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን እያስተናገደች ያለች አካባቢ እንደሆነችና ለአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ክልልም ጭምር ትልቅ አቅም ሊሆኑ የሚችሉ ሀብቶችን በቱሪዝም ዘርፍ ያቀፈች በክልሉ ውስጥ ካሉ ሌሎች አካባቢዎች ጋር ተመጣጣኝ የእድገት ደረጃ ላይ ያለች ቢትሆንም ካለበቂ ምክንያት መገለሏ ህዝብን እንዳስከፋቸው ተናግረዋል።


በአመያና በጪዳ ከተማ ዞረን ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎቹ አያይዘውም ብልጽግና ፓርቲ ዓላማውና ራዕይው አቃፊ፣ አካታችና ፍትሃዊነትን የሚከተል እንደሆነ ግልፅ ቢሆንም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአግላይነት አካሄድን ከወዲሁ እየተለማመደ መገኘቱ ቀጣይ የህዝብን አብሮ የመልማትና አብሮ የመበልፀግ ተስፋ ላይ መተማመን እያሳጣ በመሆኑ መንግስት ውሳኔዎችን በጥልቀትና መልሶ እንዲያጠን ሲሉ ጠይቋል። ዘገባው ኮ/ዞ/መ/ኮ/ጉ መምሪያ ነው!
