“ሕብረ-ብሔራዊ ተቋም ግንባታ በማጎልበት የአስተሳሰብና የድርጊት ሌብነትን በመታገል ለመማር ማስተማር ምቹ ሁኔታ በጋራ ለመፍጠር እንተጋለን” – ፕሮፌሰር ታከለ ታደሴ

የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ከመምህራና እና ቴክኒካል ረዳቶች ጋር በመልካም አስተዳደር እና በልማት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል።

ለትምህርት ጥራት እውን መሆን የመምህራንን መሰረታዊ ፍላጎት ማረጋገጥ ተገቢ እንደሆነም በምክክር መድረኩ በስፋት ተጠቁሟል።

ከዩኒቨርሲቲው መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች ጋር በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ የተገኙት የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ መልካም አስተዳደርን በማስፈን ሠላማዊ መማር ማስተማርን ማረጋገጥ እና ማዝለቅ የቅድምያ ቅድምያ የሚሰጠው ተግባር ነው ሲሉ ተናግረዋል።

መምህር የሰውን ልጅ የሚያንጽ የእውቀት ነጸብራቅ እንደሆነ የተናገሩት ፕ/ር ታከለ ታደሰ፤ በእውነት ላይ በመቆም ለሕብረተሰብ ዘላቂ ለውጥ እውን መሆን በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ የማህበረሰብ አገልግሎት ላይ መሰማራት ከሁላችም ይጠብቅማል ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም፤ መልካም አስተዳደርን ማስፈን፥ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ፥ በተቋም ደረጃ የተጀመሩ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ፥ ሕብረ-ብሔራዊ ተቋም ግንባታን ማጎልበት፤ እንዲሁም የአስተሳሰብና የድርጊት ሌብነትን በጽናት መታገል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በቀጣይ ይተገበራል ሲሉ ተናግረዋል።

በምክክር መድረኩ “የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ቋሚ ሠራተኞች የባንክ ብድር አገልግሎት የውስጥ አሰራር መመሪያ ቁጥር 023/2014” በዩኒቨርሲቲው መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት መ/ር ሀርቆ ሀላላ የቀረበ ሲሆን፤ “የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የጋራ መኖርያ ቤቶች አስተዳደር የውስጥ አሰራር አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 002/2014” ገለጻ በመምህርት ንግስቴ አበበ ቀርቧል።

በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዘርፎች በሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ እና በቀረቡት ሰነዶች ዙርያ ከተሳታፊዎች አስተያየትና ጥያቄ ተነድቶ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄና አስተያየቶች የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ፤ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ዴአ እንዲሁም የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መስፍን ቢቢሶ ምላሽ ሰጥተዋል።

እንደ ዩንቨርስቲው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዘገባ ለትምህርት ጥራት እውን መሆን የመምህራንን መሰረታዊ ፍላጎት ማረጋገጥ ተገቢ እንደሆነ እና ለዚሁም የዩኒቨርሲቲው አድተዳደርር ተገቢውን ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ፈጣን ምላሽ ለመድጠት ዝግጁ መሆኑ በምክክር መድረኩ በምክክር መድረኩ ተጠቁሟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: