የአየር ንብረት መለዋወጥን እና የዝናብ መቆራረጥ እና መዘግየትን ተከትሎየጤና ስጋቶችን በመለየት ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገባ የዎላይታ ዞን ጤና መምሪያ አስተውቋል ።

የዎላይታ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ አሳምነው አይዛ በመልዕክታቸው የዝናብ መቆራረጥ እና መዘግየትን ተከትሎ ወባ፣ የምግብ እጥረት እና ኮሌራ እንዲሁም በእነዚህና በሌሎች አጋጣሚዎች የኩፍኝ ወረርሽኝ በሁሉም አከባቢ ከፍተኛ የጤና ስጋት በመሆኑ የመከላከል፣ የመቆጣጠር፣ ዝግጁነት እና ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በዚህም ረገድ የተለያዩ ድንገተኛ አደጋዎችን ቅኝት፣ መቆጣጠርና ምላሽ በመስጠት ረገድ በየደረጃው እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በዝርዝር ተገምግሟል በዚህም የምግብ እጥረት ኮሌራ እንዲሁም የኩፍኝ ወረርሽኝ በሁሉም አከባቢ ከፍተኛ የጤና ስጋት በመሆኑ የመከላከል ይገባል አሳብም ተመላክቷል፡፡

ለችግሩ ክብደት ተሰጥቶ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ባለሙያዎች የየዕለት አጀንዳ አድርጎ መምራት ይጠበቃል ያሉት የመምሪያ ሀላፊ የመከላከሉን ሥራ በንቅናቄ የመምራትና ፣የግብዓት አቅርቦት ፣እስከ ጤና ኬላ ድረስ በበቂ ሁኔታ መኖሩን ክትትል ማድረግ እንደሚገባ በማስገንዘብ ችግሮቹን ለመቆጣጠር እና ሊገጥሙ የሚችሉ የጤና ስጋቶችን ለማስቀረት ህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ የአጋር ድርጅቶች ሊጎለብት እንደሚገባው አስገንዝበዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: