
በትናንትናው ዕለት የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ “የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ልዩ ድምቀት” በሚል የዎላይታ ዲቻ እግርኳስ ደጋፊዎችን አሞካሽቶ መረጃውን አጋርቶ ነበር።
ያንን ተከትሎ ሚዲያው መረጃውን በማጋራቱ በርካታ ሰዎች በማጋራትና ሀሳብ ተሳትፈዋል። ቢሆንም ከጥቂት ሰዓታት በኃላ መረጃውን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አጥፍቶታል።

በርካታ ሰዎች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ “የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከይፋዊ ፌስቡክ ገፁ መረጃውን ለምን እንዳነሳ በጠየቁት መሠረት ምላሽ አግኝተናል።
በጉዳዩ ዙሪያ የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ማህበራዊ ሚዲያና ዌብሳይት ዳይሮክቶሬት ዳይረክቴር የሆኑትን አቶ ዳዊት ሽፋራው በሰጡት ምላሽ መረጃውን ከሚዲያ እንዲነሳ መደረጉን አስረድተዋል።

እንደ ዳዊት ገለፃ መረጃውን የለጠፈው የዕለቱ ተረኛ ጋዜጠኛ መሆኑን በማስረዳት የተለጠፈው መረጃ ደግሞ ከሚዲያ አንፃር ትክክል ባለመሆኑ ነው ብለዋል።
“ሚዲያው ሲዳማን፣ ደቡብ ምዕራብ እንዲሁም አሁን ያለውን ደቡብ ክልልን እኩል የሚያገለግል በመሆኑ በተለየ መንገድ የዲቻን ማጋራት የለብንም በሚል እንዲነሳ አድርገናል” በሚል አክለው አቶ ዳዊት ተናግረዋል።
የዎላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ በሀገሪቱ በርካታ ደጋፊዎች የምታወቅ የህዝብ ክለብ ነው። ከትናንት ወዲያ በአዳማ እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ አቻውን የገጠሙት የዎላይታ ዲቻ ስፖርት ቡድን በደረጃ አናት ላይ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ የሚያስችል ውጤት አስመዝግቧል። ከሊጉ መሪ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት በማምጠብ በ31 ነጥብ ሊጉን በሁለተኛነት መምራት በመጀመር ዋንጫውን ለመውሰድ ጠንካራ ተወዳዳሪ እየሆኑ መሆኑ ይታወቃል።

What is your responsibility with regard to WRS or wolaita Regional state? And why the ethiopia government does not give attention to our question?