FB_IMG_1649172149174

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ከዎላይታ ዞን ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር የወባ በሽታ ለማጥፋት ይፋ ማድረጊያ መድረክ በዎላይታ ሶዶ ተከናውኗል።

ከወባ በሽታ የጸዳች ኢትዮጵያን መፍጠር ግብን ዕውን ለማድረግ በዞን ደረጃ የሚከናወኑ ተግባራት አፅንዖት የሚሹ በመሆናቸው የወባ በሽታ ከዎላይታ ዞን ማጥፋት ይቻላል ዘመቻን አስመልክቶ በጋራ በመምከር በቀጣይ የታቀዱ ስራዎችን ለማመላከት ታሳቢ ያደረገ መድረክ መሆኑ ተገልጿል፡

የጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ሃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ሃላፊ አቶ መና መኩሪያ በመልዕክታቸው በ2023 ከወባ ነፃ የሆነች ኢትዮጲያን ዕውን የማድረግ ራዕይን ለማሳካት እንደ ክልል ብሎም እንደ ዞን ሚደረጉ ጋራ ርብርቦች  ሁሉም ዜጋ ወባን በማስወገዱ ረገድ ድርሻ እንዳለው ማስገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡

ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ህመምና ሞት ምክንያት የሆነው የወባ በሽታ መቀነስ መቻሉ ብሎም መቀመጡ አበረታች ቢሆንም ተግባራት ወባ አሁንም የጤና ስጋት የሆኑባቸው አከባቢዎች መኖራቸው ተጠቅሷል።

የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በበኩላቸው  ወባን ጨርሶ የማጥፋት ራዕይ በዞን ደረጃም እውን በማድረግ በሽታዎች በህብረተሰቡ ላይ የሚያደርሱትን የጤና ችግሮችን ለመከካል የሚየስችል ተግባርን ለመፈጸም የሚችል መሆኑን ተናግረው  በዚህ ረገድ የሀይማኖት አባቶች፣ የአመራሩና የሀገር ሽማግሌዎች ጭምር ሚናቸውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።

የወባ በሽታ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት ከወሬ ይልቅ በተግባር የሁሉም እርብርብ እንደሚያስፈልግ የዎላይታ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ አሳስበዋል።

የዎላይታ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሳምነው አይዛየወባ በሽታ  ጤና ላይ የሚደርሰዉን ተፅዕኖ መቀልበስ በበሽታው የሚያዙ ህሙማን ቁጥርም ሆነ በወባ ሳቢያ የሚሞቱ ዜጎች ቁጥር በእጅጉ መቀነስ ብሎም ወባን በማስወገዱ ረገድ ውጤታማ እንዲሆን ህብረተሰቡን የቁጥጥር ስራው ባለቤት በማድረግ ተግባርን አቀናጅቶ በመመራት ተጠባቂ መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩ አቶ መና መኩሪያ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ አስተባባሪ፣ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ እንዲሁም ሌሎች የዞን እና የወረዳዎች የመንግስት አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል።