FB_IMG_1649920071551

ሆቢቻ ወረዳ ኤሎ እራሾ ቀበሌ ቡቅሳ ቀጠና ላይ ድንገተኛ የሞት አደጋ ተከስቷል።

በዎላይታ ዞን ሚያዝያ 04/2014 ዓ/ም በሆቢቻ ወረዳ ኤሎ እራሾ ቀበሌ ቡቅሳ ቀጠና ላይ የአንድ እንቨስተር ማሣ ላይ የዝናብ ምክንያት መብረቅ ወርዶ የአጥር ግንብ ተደርምሶ የሁለት ሰዉ ሕይወት ማለፉንና ፣ በአንድ ሰዉ ላይ ከባድ የአካል ጉዳትና ሁለት ሰዉ ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መደረሱን ያገኘው መረጃ መረዳት ተችሏል።

አደጋው መንስኤዉ የዝናብ ምክንያት መብረቅ ወርዶ የአጥር ግንብ ተደርምሶ የሁለት ሰዉ ነፍሰ ማጥፋቱንና በሁለት ሰዉ ላይ ቀላል አካል ጉዳትና በአንድ ሰዉ ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን በጠቅላላ 5 ሰዉ መሆኑን የደረሰ ተጨባጭ መረጃ መረዳት ተችለዋል። አደጋው 11:30 ሣዓት አከባቢ መሆኑን ያረጋገጠው ፖሊስ አዛዥ መቶ አለቃ ሕዝቅኤል አይዳ ናቸው።

መ/አ ሕዝቅኤል እንዳሉት ማንኛዉም ሰዉ በዝናብ ወቅት ከቤት ወጥቶ በትልቅ ባህርዛፍ ፣በሾላ ወስጥና አላሰፈላጊ ቦታዎች ላይ ጥንቃቄ መዉሰድ እንዳለበት አሳስበዋል።

1 thought on “በዎላይታ ዞን ሆብቻ ወረዳ መሬት ተደርምሶ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ”

Comments are closed.