በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንታ ዞን ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር ባሳ በየነ እንደገለፁት በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ሴሬ ቀበሌ ሚያዚያ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት 4:00 ሰዓት አንድ ግለሰብ በእርሻ ማሳዉ የቤት መስሪያ እንጨት እየሰበሰበና በቆሎ ማሳዉን እየጠበቀና ለቤት መስሪያ እንጨት በባትሪ እያሰባበ እያለ ዝሆን በቆሎዉን ሊበላ ሲሞክር ዝሆኑ ግለሰቡን በኩሚቢው በመያዝ በእግሮቹ ርግጦ ህይወቱ እንዲያልፍ መድረጉን ተናግረዋል።

ከአንድ አመት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ አንድ አርሶ አደር በጎሽ ተወግቶ ህይወቱ ማለፋን ገልፀዉ ህ/ሰቡ በእርሻ ማሳ የእጅ ባትሪ ከመጠቀም መቆጠብ እንዳለባቸዉ የገለፁት አዛዡ አክለዉም የዱር እንስሳት በሚያጋጥምበት ወቅት ከተቻለ በህብረት አልያም መሸሽ እንዳለባቸዉ ጠቅሰዉ የዘርፋ ባለሙያዎች በጉዳዩ ዙሪያ ጥናት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የዘገባዉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ገፅታ ግንባታ ነዉ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: