

መጋቢ ዮሐንስ ባሣና የክብር ዶክትሬት ድግሪ በወንጌል አገልግሎት ዘርፍ ከገሊላ ኢንተርናሽናል ሴሚናሪ መቀበላቸውን ከቤተክርስቲያኗ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
መጋቢ ዮሐንስ ባሳና በወጣትነት ዕድሜዎ “ያኒድ ጋካና” በሚለው ዝማሬ የጀመሩትን አገልግሎት እግዚአብሔር በታላቅ ሞገስ አጅቦ በጸጋው ሸፍኖ በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ በተለያዩ አገሮች የተጉ በቤተክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው መንፈሳዊ ሰው መሆናቸው ይነገርላቸዋል።

በተላይም በዎላይታና አከባቢው ስለ ወንጌል መልዕክተኝነት በብዙ መከራና ስደት አልፈው በማገልገልና በታማኝነት ምሳሌያዊ አገልግሎት በመስጠት የሚታወቁት እኚህ መንፈሳዊ አባት በሰማይ ብቻ ሳይሆን በምድር ላይም በክብር በሽልማት እንዲያጠናቅቁ ለዚህ የክብር ሽልማት ቀን ያበቃዎት እግዚአብሔር ምሥጋናና ክብር ይገባል ስሉም ቤተክርስቲያንቷ ደስታውን ገልፃለች።
Gashen eniwodalen enakebiralen