የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ዘመን መለወጫ የፊቼ ጫምባላላ በዓልን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር እንዲያስችል ለበዓሉ አከባበር ለቅድመና ድህረ ዝግጅት ሥራ የተዋቀረው አብይ ኮሚቴ ሥራን ገመግሟል።

የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ የሆነው ፊቼ ጫምባላላ የአለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን በደማቅ ሁኔታ በአደባባይ በታላቁ ጉዱማሌ የሚከበር በዓል ነው አባቶችም ከጥንት ጀምረው የዘመን መለወጫውን አድስ ዓመት በማክበር ለትውልድ ስያስተላልፉ የኖረ ስወርድ ስዋረድ የመጣ በዓል ነው።

ይሁን እንጂ ላለፉት ለ2 ዓመታት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህዝቡ በየቤቱ ያከበረ ቢሆንም በአደባባይ ሳይከበር አልፏል። በዘንድሮው ዓመት ግን የፊቼ ጫምባላላ በዓልን በአደባባይ በታላቁ ጉዱማሌ በደማቅ ሁኔታ በሚያዚያ 20 እና 21 ለማክበር የተለያዩ ኮሚቴ ተዋቅሮ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቅቋል።

የፊቼ ጫምባላላ በዓል ያለ ምንም ፀጥታ ችግርና በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የአብይ ኮሚቴ የደረሰበትን የቅድመ ዝግጅት ሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሂደዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አፈፃፀሙን በገመገሙበት ወቅት በዓሉ በሲዳማ ብሔር ዘንድ ትልቅ ቦታ ያለውና ከሰው ልጆችም አልፎ ለእንስሳት እንዲሁም ለፍጥረት ልዩ ቦታ የሚሰጥበት በዓል ነው ብሎ ዘንድሮ ክልል ከሆንን ወዲህ በደማቅ ሁኔታ በታላቁ ጉዱማሌ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት በሚያዚያ 20 እና 21 ይከበራል ብለዋል።

በዓሉ በውስጡ ከያዛቸው እሰቶች ውስጥ አንድነትና መዋደድ ስሆን በዓሉን ስናከብር በህብረትና እርስ በርስ በመዋደድ መሆን ይገባል ብለዋል። ይሄ በዓል የተጣላው የሚታረቅበት፣ እንስሳት የማይመታበት፣ እርድ የማይፈፀምበት፣ ዛፍ የማይቆረጥበት በዓል በመሆኑ በፊቼ ጫምባላላ እሴት መሠረት በዓሉን ማክበር ያስፈልጋል ብለዋል።

ጨምሮም ፊቼ ጫምባላላ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት የማያስፈልገውና ለቢዝነስ ግብዓት የሚውል አይደለም ይህም ፊቼ ጫምባላላ በዩኔስኮ ስመዘገብ እነዚህ እሴቶች በውስጡ ተካቶ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም በማለት ህዝቡ በዓሉ የራሱ የህዝቡ ስለሆነ ፀጥታውን ህዝቡ እንዲጠብቅና መንግሥትም በተጨማሪ ፀጥታውን ለመጠበቅ በቂ ዝግጅት አድርጓል ብለዋል ሲል የሲዳማ ብ/ክ/መ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: