

ለይበልጣል ኤሊያስ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር አንድ ሚሊየን አምስት መቶ ሺህ ብር ሰጠ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ባርሴሎና ከተማ በሚገኘው B1 አካዳሚ ለሚሰለጥነው ታዳጊ ይበልጣል ኤሊያስ ለአካዳሚ ክፍያ የሚሆን የ1,500,000(አንድ ሚሊየን አምስት መቶ ሺህ ብር ስጦታ አበርክቷል::
የሊግ ካምፓኒው ቦርድ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃፈቃደ ማሞ ይበልጣል ወደፊት በትልቅ ደረጃመጫወት ሲጀምር የሚመልሰው ‘ኢንቨስትመንት’ እንደሆነ ገልፀዋል::
ይበልጣል ሩቅ በማይባል ጊዜ በባርሴሎና ወይም ሪያል ማድሪድ ክለቦች የመጫወት አቅም እንዳለውና ለኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች በር የመክፈት ፍላጎት እንዳለው ተናግሯል ስል ጋዜጠኛ አወቀ አብራሃም መረጃውን አጋርቷል።