የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞ፤ ባለፉት ዓመታት የተስተናገዱ ማህበራዊ ኢኮሚያዊና ፖለቲካዊ ፍኖት የሚቃኝ ድንቅ መጽሐፍ መሆኑ ተመስክሮለታል፡፡

በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የተፈጠረው ጦርነት፤ በሌሎች አካባቢዎች የተከሰቱ ፖለቲካዊ ትኩሳቶች እና የዎላይታ ህዝብ ከለውጡ መምጣት ጋር ተያይዞ የገጠመው የፖለቲካ ፈተና ከመፃኢ እድሉ ጋር ተሰናስሎ የቀረበበት መፃህፍ ነው።

በአስቸጋሪው የ4 ዓመታት ጉዞ ከፖለቲካው ባሻገር የነበሩ ሴራዎች፤ ፈተናን የሚያሻግሩ የኢትዮጵያውያን እሴቶች፤ የፖለቲካው የሀይል ሚዛን ዝንፈቶችና ምላሽ ያላገኘው የህዝቡ ጥያቄ መምረር በጥሞና ተዳስሶበታል፡፡

በፖለቲካና የመንግስት አስተዳደር ውስጥ የዳበረ ልምድ ባካበቱት ብስለት በተሞላው አገራዊ ጉዳዮች ቅኝታቸው በሚታወቁት በደራሲ ዋዱ ዳና የተዘጋጀ የገሃዱ ዓለም እውነታ መጽሐፍ፡፡

ፖለቲከኞች፣ ምሁራን እና ወቅቱን መዋጀት የሚፈልጉ ወጣቶች ቢያነቡት ይመከራል፡፡ ህትመትና ዲዛይን ዛክ ማተሚያ ቤት ጥራትን በጠበቀ ደረጃ ተሰርቷል።

አከፋፋይ አስራት መጽሐፍት መደብር በዎላይታ ሶዶ መናሀሪያ አከባቢ ያገኛሉ።መጽሐፉን ማከፋፈል የምትፈልጉ በስልክ ቁጥራችን 0911006457 ወይንም 0905444171 ይደውሉልን፡፡

ውስብስቡ መንገድ በገበያ ላይ፤ በተመረጡ መጽሐፍት መደብር ያገኙታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: