የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ኮሌጁ የተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አልፎ ለምረቃ መድረሱ በልዩ ሁኔታ እንዲመረቅ አድርጎታል ብለዋል።

የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሠልጣኞች  አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ክህሎታቸው በማሳደግ  ወደ ተግባር እንዲቀይሩ የሚረዱ ተቋማት መሆን አለባቸው ብለዋል።

የሰላምበር ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅን ጨምሮ በዞኑ ውስጥ ስምንት ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን ቀሪ መስፈርት በሟሟላት ላይ ያሉ ኮሌጆችን ከክልሉ ጋር ተነጋግሮ  በመክፈት  ብቃት ያላቸውን ሠልጣኞች ለማፍራት እየተሰራ መሆኑን አቶ ብርሃኑ ገልጸዋል።

የኮሌጁን ደረጃ ለማሻሻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ አቶ ብርሃኑ ያሳሰቡ ሲሆን እንደ ሀገር ትልቅ ሕዝቦች የሆንበትን የሠላም እሴት ማስቀጠል አለብን ብለዋል።

የጋሞ ዞን አስተዳደር ኮሌጁ ያሉበትን ጉድለቶች እንዲያሟላ ከዘንድሮ በጀት 500 ሺህ ብር እና ከቀጣይ በጀት ዓመት  1ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል ።

የሠላምበር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ማቴዎስ ማይዛ  በህብረተሰብ ተሳትፎ ለትምህርት ማስጀመሪያ የሚሆን ሕንጻ በ4 ሚሊዮን ብር ከተገነባ በኋላ በገበያ ንረት ተስተጓጉሎ በዘንድሮ በጀት ዓመት 68.8 ሚሊዮን  ብር  ግንባታውን እንዲጠናቀቅ  ተደርጓል ብለዋል።

ከከተማው ማህበረሰብ ለ3 ቀናት በተደረገ ንቅናቄ ለስልጠና ግብዓት ማሟያ 573 ሺህ 995 ብር ገቢ መሰብሰቡን አቶ ማቴዎስ ተናግረዋል ።

የሠላምበር ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ  ዲን አቶ ድርጅት ድንበሩ ኮሌጁ  የመማሪያ ፣ የአስተዳደር ፣ አዳራሽ ፣ ቤተመጻሕፍት ፣ የማምረቻ ክፍሎች  ያሉት መሆኑን ገልጸው የውስጥ ቁሳቁስ በማሟላት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሌጁ በ2014 ትምህርት ዘመን 681 ተማሪዎችን በ6 የስልጠና ዘርፎች እያሰለጠነ ሲሆን በ2015 ዓ.ም በሙሉ አቅሙ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን መዘጋጀቱን አቶ ድርጅት ተናግረዋል ስል የጋሞ ዞን መ/ኮ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: