አረካ ከተማ ባሁኑ ሰአት በአልጋ እና ምግብ እዳ ምክንያት መሄድ በነበረባቸው ሰአት ወደ ከተማቸው መመለስ ሲኖርባቸው ባሁኑ ሰአት በክለቡ የበላይ ጠባቂዎች ቱኩረት ማጣት በእዳ ድሬዳዋ ከተማ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል።

የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ምድብ ሐ ሻምፒዮን የሆነው የአረካ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ተጨዋቾች በአሁን ሰአት በድሬዳዋ ከተማ በችግር ውስጥ እንደሚገኙ ከተጫዋቾቹ እና ቤተሰቦቻቸው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጀ ያመለክታል።

በ2014 ዓም የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ በምድብ ሐ ተደልድለው አንደኛ ዙር በአሰላ ከተማ ሁለተኛ ዙር በቡራዩ ከተማ ውድድራቸውን በማድረግ የምድቡ ሻምፕዮን በመሆን ወደ ማጠቃለያ ውድድር በማለፍ ድሬዳዋ የከተሙት አረካ ከተማ አሁን ላይ በችግር ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አረካ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በወጣቱ አሰልጣኝ እየተመራ በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር በድሬዳዋ ከተማ ክስተት እና የተሻለ ቡድን ሁኖ የቀረቢ ሲሆን በስተመጨረሻ አሳዛኝ ተሰናባች በመሆን በዞኑ ሌላኛው ክለብ ቦዲቲ ከተማ ተሸንፎ ከምድቡ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል። ከውድድሩ መውደቅ በተጨዋቾች የሚፈጥረው ስሜት እንዳለ ሁኖ ተጨዋቾቹ ሁለተኛ ሞራላቸው የተነኩበት ክስተት በክለቡ የበላይ ጠባቂ ገጥሟቸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የከተማ ከንቲባ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ያልተሳካ መሆኑን እየገለፅን የአረካ ከተማና የዎላይታ ዞን አመራሮች ተጫዋቾች ያሉበት ችግር ተረድታቹህ ካሉበት ችግር እንድታወጧቸው እንላለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *