የደቡብ ክልል ዎላይታ ማዕከል አመራሮች በዎላይታ ኦሞ ሰው ሰራሽ ኃይቅ ጨምረው ሌሎች የልማት ስራዎችን ጉብኝት አደረጉ

በደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በአቶ ይሁን አሰፋ የተመራው የክልሉ ከፍተኛ አመራር ቡድን በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በዛሬው ዕለት ተመልክቷል።

በዎላይታ ሶዶ ማዕከል ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ  የሚገኙ የእርሻ ስራዎችን ተዘዋውረው የጎበኙት።

የግልገል ግቤ-3 ኤሌክትሪክ ማመንጫ ኃይል መገንባት ተከትሎ የተፈጠረው የዎላይታ ኦሞ ወንዝ ሰው ሰራሽ ኃይቅ ላይ ዓሳ የማልማት ስራ ከፍተኛ ውጤት  እያስገኘ መሆኑን አመራሮቹ ጎብኝተዋል።

በኃይቁ ከዓሳ ልማት ስራ በዘለለ ውሀ ላይ ትራንስፖርት አገልግሎት እና አካባቢውን የቱርስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑንም አመራሮች ተመልክተዋል።

በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ ግል ባለሀብቶች ሙዝን ጨምሮ ሌሎች የአትክልትና ፍራፍሬ በማልማት ረገድ የተሻለ ምርት መኖሩንም አመራሮቹ መመልከታቸውን የወረዳው ዘገባ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: