“አካታች ብሔራዊ ምክክር ለዘላቂ ሰላማችን፣ ለአብሮነታችንና ለብሔራዊ መግባባታችን” በሚል ሀገራዊ የፓናል ውይይት በወላይታ ዩንቨርስቲ ተካሄደዋል ።

የውይይት መድረኩ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ከኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር እና ከደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር ነው የተዘጋጀው።

የዎላይታ ዩንቨርስቲ ፕረዚዳንት ፕሮፈሰር ታከለ ታደሰ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉት ወቅት እንዳሉት ዩንቨርስቲው አገርን በአመለካከት፣ በዕውቀትና በክህሎት የሚገነባ ትውልድን ዜጎችን ለመፍጠር እየሰራ ነው።

ዩንቨርስቲው ጽዱ፣ አሬንጓዴና ሰላማዊ በማድረግ አገር አቀፍ ተቋማዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

የኢፈዲሪ ሰላም ሚኒስተር ሚኒስተር ደኤታ አቶ ታዬ ደንደኣ እንደተናገሩት አካታች ምክክር መድረኩ የአገራችንን ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለማረጋገጥ ይስችላል።

በመመካከር፣ በመተባበርና በመደማመጥ መንፈስ እጅ ለእጅ ተያይዘን ሁለንተናዊ ብልፅግናችንን ለማረጋገጥ መትጋት ያስፈልጋልም ብለዋል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት አገር በቀል ባህላዊ እሴቶች ለአገር ሰላም ያለው ፈይዳ የጎላ ነው።

አገራዊ አንድነታችንን በማጠናከር የብልፅግና ጉዟችንን ማስቀጠል አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው ብለዋል።

የአሁኑ ትውልድ ከቀደምት አባቶቻችን የተረከቡትን አገር ለማሻገር ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በውይይት መድረኩ የብሔራዊ ምክክር ፅንሰ ሃሳብ፣ አስፈላጊነት፣ ተሞክሮዎችና ኢትዮጵያ ልትቀስማቸው የሚገቡ ልምዶች እንዲሁም የእምነት ተቋማትና በህላዊ እሴቶቻችን ሚና ለሀገራዊ ምክክር በሚል ርዕሶች ጥናታዊ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተካህዶባቸዋል።

ጥናታዊ ጽሑፎቹ የቀረቡት በዶክተር አልማው ክፍሌ በኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩንቨርስቲ የህግና ታሪክ ተመራማሪ እና በዶክተር አብዱ ሙሀመድ በዲላ ዩንቨርስቲ የታሪክ ተመራማሪ አማካይነት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *