የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከኤስ.ኤን.ቪ ራይ( SNV RAYEE Project) ከተባለ አለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር ይህን የስራ ማስታውቂያ ቦርድ በቅርብ ጊዜ ተግባራዊ እንደሚያደርገው ታውቋል።

በከተማው የሚስተዋለውን ህገወጥ የስራ ማስተውቂያ አሰራርን በማስቀረት ፍትሃዊ የማስታወቂያ ተደራሽነትንና አገልግሎትን በጥራት ተግባራዊ ለማድረግ አስቻይ መሆኑም ተጠቁሟል።

በከተማው ሆነ በአከባቢው ህጋዊ የስራ ማስታወቂያ ቦርድ ባለመኖሩ ህብረተሰቡ በተለያዩ ቦታዎች ባልተደራጀ ሁኔታ የሚለጠፉ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን የማግኘት ዕድል አነስተኛ በመሆኑ ለተጠቃሚዎች እንቅፋት ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

የተለያዩ የስራ ማስታውቂያዎች በተለይም የጨረታ ማስታወቂያዎች፣ የፍርድቤት ጥሪ ማስታውቂያዎችና ሌሎች ማስታወቂያዎች በከተማዋ በተደራጀ ሁኔታ «በማስታወቂያ ቦርድ» ባለመለጠፉ ተገቢ ጥበቃ ስለማይደረግ ለተጠቃሚዎቹ ሳይደርስ የመበላሸት፣ የመቀደድ እና ሆን ተብሎ ያለግዜ የመነሳት ሁኔታዎች በመኖሩ አሁን በቅርቡ ስራ የሚጀምረው የተደራጀ የስራ ማስታወቂያ ቦርድ ችግሩን ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በከተማዋ ለህብረተሰቡ በቀላሉ ተደራሽ በሚሆኑ ሶስት ቦታዎች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ህጋዊ ፈቃድ በመወሰድ ስራውን በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ለመጀመር እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

ይህ ተግባር ከማስታወቂያ አገልግሎት ጎን ለጎን የተለያዩ የጨረታ ጋዜጦች የሚያገኙበት ሁኔታ ያመቻቸ ሲሆን በዚህም እስከ ስድስት ለሚደርሱ ወጣቶች የስራ ዕድል ይፈጥራል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከኤስ.ኤን.ቪ ራይ (SNV RAYEE Project) ከተባለ አለምአቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በትብብር ከሚያሰራው የስራ ማስታውቂያ ቦርድ (Offline Job Board) በተጨማሪ በሚዲያው ዌብሳይ እና ማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ቋሚ ማስታውቂያ ቦርድ (Online Job Board) አማራጭ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጀቱን እየጨረሰ እንደሚገኝ በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *