ዎላይታ ሶዶ ከተማ የ130 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋዋ፣ የዳሞት ፀዳሏ፣ ባለ ግርማ ሞገሷ፣ ጥንታዊነቷም ሆነ ዘመናዊነቷ የሚያኮራት፣ በኢትዮጵያ ብቸኛዋ ባለ 7 በር ከተማ፣ የመላው ኢትዮጵያውያን ሆነ የውጫዊያን አብረው የመኖር ተምሳሌቷ፣ ከባህር ጠለል በላይ ከ 2400 ሜ. በላይ ከፍታ ላይ ሆና እንኳን ለሰው ዘር ለአእዋፍ እና እፅዋት ተስማሚ የሆነችዋ፣ በክልሉ ብቸኛው በራሷ ገቢ የሚተዳደር 🙏

ለሁሉም አከባቢዎች አማካይ ርቀት ላይ ያለችው ይህች ከተማ የብዙዎችን ቀልብ በመሳብ ፈጣን ዕድገት እያሳየች ከራስጌዋ ትልቁን የዳሞታን ተራራ እንደ ሻኛ ተንተርሳ ያለች ስትሆን ከባህር ጠለል በላይ 1600 ሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች።

ይህች ከተማ ከሀገራችን መድና አዲስአበባ በቡቴጂራ መንገድ በ330 ኪ.ሜ ርቀት እንዲሁም በሻሸመኔ መንገድ በ390 ከ.ሜ ርቀት በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ የሚትገኝ ሕበረብሔራዊት ከተማ ነች::

ከጊቤ(ኡማ) 3 ሰው ሰራሽ ሀይቅና ከዐባያ ሀይቅ መሀከል የሚትገኘው በተፈጥሮ የታደለች ከተማ ፣ የአባያ ሀይቅ ውበት ከዳሞታ ተራራ ውበትን ያደመቃት፣ የውስጥ ለውስጥ 50 ኪ. ሜ. በላይ አስፋልት መንገድና ከ70 ኪ.ሜ. በላይ በገጠኛ ድንጋይ የተዋበች፤ ከምንም በላይ የሰው ፍቅር ያላት አብሮ መብላት አብሮ መጠጣት ብቻ ሳይሆን በተግባር ኢትዮጵያዊ የመረዳዳት ባህል ያላት ዎላይታ ሶዶ ከተማ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ቤት መሆኗ ለየት ያደርጋታል።

ከተማዋ በቅርብ ጊዜ ፈጣን ዕድገት ካሳዩ ከሀገራችን ከተሞች በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች፡፡

ለከተማ ዕድገት በወሳኝነት የሚያስፈልጉትን መብራት (በኦሞ(Uma) ወንዝ የተሰራው የጊቤ 3 ግድብ power station መገኛ፣ ውሃ (በቅርቡ አገልግሎት መስጠት የጀመረውና ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት የከተማዋን ፍጆታ የሚያሟላው የሊቅምሴ water project መገኛ)፣ የተለያዩ ባንኮች፣ እንሹራንስ፣ ትምህርት ተቋማት እንዲሁም ስልክ (ኢትዮ ቴሌኮም የደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጂን) መገኛ ነች::

በጤናው ዘርፍ ፈር ቀዳጅ የሆነው በ1926 የተቋቋመው የቀድሞ ኦቶና የአሁኑ ኦቶና Comprehensive Specialized Hospital እንዲሁም ከኢትዮጵያ አልፎ በምስራቅ አፍሪካ ስምና ዝናን ያተረፈው በተላይ በአጥንት ቀዶ ጥገና በስፍት የሚታወቀው የSodo christian Hospital ሌሎች ጤና ጣቢያዎች እና በርካታ የግል ክሊኒኮች በስፋት ይገኙባታል፡፡

መቼስ መንገድ የሰዎችን ና የንግድ እንቅስቃሰ ለማሳለጥ እጅግ የሚያስፈልግ ደምሥር እንደሆነ የማይካድ ሀቅ ነው፡፡

እናም ይህን የተረዳችው የሶዶ ከተማ ከ145 ኪ.ሜ የሚበልጥ የጥርጊያ ፣ የ58 ኪ.ሜ የጌጠኛ ንጣፍ እንዲሁም የ42.5 ኪ.ሜ የአስፋልት መንገድ ባለቤት ነች፡፡ በአለምባንክ ድጋፍ ከፍተኛ በጀት በማግኘት የተለያዩ መሠረት ልማትን በቀዳሚነት እየሰራች የምትገኝ ከተማ።

በአቅራቢያው ለሚገኙ የደቡብ ክልል አከባቢዎች በአማካይ ቦታ ያለች ስትሆን ከነዚህም እህት እና ወንድም ሕዝቦች ጋር በቀጥታ የሚያገናኟት 7 የመዉጫ እና መግቢያ በር ያላት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ከተማ ነች፡፡ ዘመናዊ የትራንስፖርት አማራጭ ለማሳለጥ የአውሮፕላን ማረፊያ በቅርቡ ስራ እንዲጀመር እየተሰራ የሚገኝባት ❤

የተለያዩ ሀገራዊ እና ክልላዊ ስብሰባዎችንና ኮንፌራንሶችን ማስተናገድ የሚችሉ ደረጃቸውን የጠበቁ አደራሾች፣ሪዞርት፣ ሆቴሎችና ፔንሲዮኖች በተሟላ ሁኔታ ይገኛሉ፡፡https://propellerads.com/publishers/?ref_id=mq3v

ኢትዮጵያን ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፓለትካዊ እንቅስቃሴዎች በነፃነት የሚጓጓዙበት ባለሰባት በር መንገዶችም⏬

  1. ከዎላይታ ሶዶ-ዋካ-ታርጫ-ጭዳ-ጅማና ከጭዳ- አመያ-ቦንጋ ኮንክሪት አስፋልት መንገድ ያላት
  2. ከዎላይታ ሶዶ- ሠላምበር- ሳውላ-ቡልቂ-ላስካ ኮንክሪት አስፋልት ያላት
  3. ከዎላይታ ሶዶ- ሁምቦ-አርምንጭ- ካራት-ጂንካ-ሳላማጎ-ሚዛን አማን የሚያገናኝ ኮንክሪት አስፋልት መንገድ ያላት
  4. ከዎላይታ ሶዶ-ባደሣ-ሞሮቾ-ዲላ-ሞያሌ -ናይሮቢ ኮንክሪት አስፋልት መንገድ ያላት
  5. ከዎላይታ ሶዶ- ቦዲት-ሾኔ-ቁሊቶ- ሻሼመኔ- ዝዋይ- አዲስ አበባ
  6. ከዎላይታ ሶዶ-አረካ-ሆሳዕና -ወራቤ -ቡታጅራ -ሰበታ አስፋልት መንገድ ያላት ናት።

7 .ዎላይታ ሶዶ- ጉልጉላ -ሆብቻ- ዲላ ጌዲኦ- ሞያሌ- ኬኒያ

ከሁሉም ኢትዮጵያዊያን ህዝቦች ጋር የጠነከረ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊና ፖሊቲካዊ ትሥሥር ያላት፤ ሶዶ ለሁሉም የአንድ አባት ልጆች የኢኮኖሚ ምንጭ ናት ማንም ሶዶን ሳይረግጥ መዋል ማደር ይከብደዋል ሶዶ ፍቅር ናት፣ተፈጥሮ ያደላት ማዕከል ላይ ናት፡፡

እናም በዎላይታ ሶዶ ከተማ ኢንቨስት እያደረጋችሁ ያላችሁ ባለሀብቶች በርቱ ተበራቱ እያልን በከተማው በአዲስ ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግና ለማልማት ለምትፈልጉ ባለሀብቶች እናንተን ለማስተናገድ ከተማዋ ሁሌም ዝግጁ እንደሆነች እንዲሁም ስራ ወዳድና እንግዳ አክባሪ የዎላይታ ሕዝብ በሚያስደምም ኢትዮጵያዊነት እጁን ዘርግቶ በፍቅር እንደሚቀበላችሁ ስነግራችሁ በደስታ ነው🙏

ኑ Invest In Wolaita, Ethiopia🙏

ሰላም ለሀገራችን🙏🇪🇹

#WolaitaTimes🤲

3 thoughts on “የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ከተሞች ለየት የሚያደርጉ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች መኖሩን ያውቃሉ ?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: