
በደቡቡ ክልል ሀላባ ቁሊቶ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ያልተገባ በአዋጅ ከተደነገገው ከ25% በላይ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ እና የሰለጠነ ባለሙያ በሌለበት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ መድሃኒት ቤቶችና መደብሮች ቅጣት ተላልፎባቸዋል።
በዚህ መሠረት በከተማዋ ሀሁ መድሃኒት መደብር የተባለ መድሃኒት ቤትየ10,000 ብር ቅጣትና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሁም ፈቃድ ያወጣ ባለሙያ እስኪመደብ አገልግሎት እንዳይሰጥ መታገዱን፣ ኢክራም መድሃኒት መደብር:- የ10,000ብር ቅጣትና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ልዑል መድሃኒት መደብር:- የ10,000 ብር ቅጣትና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ አሌክስ መድሃኒት ቤት:- የ10,000 ብር ቅጣትና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
በተጨማርም በከተማው ሲቲና መድሃኒት መደብር:- የ10,000 ቅጣት የፅሁፍ ማስጠንቀቂያና ፈቃድ ያወጣ ባለሙያ እስኪመደብ አገልግሎት እንዳይሰጥ የታገደ ሲሆን ሴሎ መድሂኒት መደብር:- ተከታታይ ጥፋት በመፈጸሙ ምክንያት የ10,000 ብር ቅጣት እና የ1 ወር የአገልግሎት እገዳና ፈቃድ ያለው ባለሙያ በህጋዊ መንገድ አምጥቶ እስኪመድብ ድረስ ፈቃዱ ታግዷል።
ስለሆነም ከላይ የታገዱ 3 መድሃኒት ቤቶች ሲቀሩ ሌሎችን የቅጣታቸውን ደረሰኝ በህጋዊ መንገድ ከፍለው በመምጣታቸው ወደ መደበኛ አገልግሎታቸው እንዲገቡ መደረጉ ተገልጿል።
በመጨረሻም ሁሉም መድሃኒት መደብሮች ከተፈቀደላቸው ከ25% ትርፍ ዋጋ ጭማር በላይ ከማድረግና ፈቃድ ያወጣ አካል በሌለበት አገልግሎት የሚሰጡና ባልተመዘገበ ባለሙያ የሚያሰሩ አካላቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን ስል የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ዘግቧል።