1659180014599

ነባር የደቡብ ክልል የዞንና የልዩ ምክርቤቶች በሁለት ክልል ለመደራጀት የሚያስችል ውሳኔ በየምክርቤቶቻቸው በዛሬው ዕለት አፀደቁ

አንደኛው በአንድ ክልል በጋራ ለመኖር የሚያስችል ውሳኔ ያሳለፉ ምክርቤቶች ዎላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ የሚገኙ ህዝቦች ደራሼ፣ቡርጂ፣ አማሮ፣ አለ፣ ጌዲኦ፣ ባስኬቶና ኮንሶ ህዝቦች በአንድ ክልል እንዲደራጁ ከውሳኔው መድረሱን ለማወቅ ችለናል።

የአደረጃጀት ጥያቄ የህዝቦችን የቆየ የአብሮነትና በጋራ የመኖር እሴት የጠበቀ እንዲሁም የህዝቦችን እኩል ተጠቃምነት በሚያረጋግጥ መንገድ እንዲሆንም የምክርቤት አባላት አንስተዋል።

በዚህም ምክርቤቱ ዎላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ የሚገኙ ህዝቦች፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ አለ፣ቡርጂ፣ ጌዲኦ፣ ባስኬቶና ኮንሶ ህዝቦች በአንድ ክልል እንዲደራጁ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ አስተያየት በመስጠት በሙሉ ድምፅ ተግባራዊ እንዲሆን አፅድቋል።

ሁለተኛው በክልል አደረጃጀት በጋራ የሚደራጁ 6 መዋቅሮች የም፣ ጉራጌ፣ ሀዲያ፣ ስልጤ፣ ሀላባ እና ከምባታ ጠንባሮ ሲሆኑ በክልል አደረጃጀት ከሌሎች አጎራባች ሕዝቦች ጋር አብሮ ለመደራጀት ወስኗል።