

ወጣት ምህረት ይልማ ከአሜሪካ አይዋ ዩኒቨርሲቲ የጆን ፓፓ ጆን የስራ ዘርፍ ምርጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሽልማት ተሸላሚ ሆነች

ምህረት ቴክኖሎጂ ተኮር በሆኑ ማህበረሰብ እገዝ እንቅስቃሴዎቿ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ እውቅናዎችን እያገኘች የምትገኝ ወጣት መሆኗ ተገልጿል።
ተወልዳ ያደገችው በዎላይታ ሶዶ መሆኑን ለ”ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” ከስፍራው ያደረሰችው ወጣት ምህረት ፦ ትውልድን ከቴክኖሎጂ ጋር የማላመድና በዘርፉ ተፅዕኖ ፈጣሪ በመሆን አለም አቀፍ ተቋም ከሆነው ከአሜሪካ አይዋ ዩኒቨርሲቲ የጆን ፓፓ ጆን የስራ ዘርፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሽልማት ላይ የ2022 የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተፅዕኖ ፈጣሪ በመሆን ሽልማት መውሰዷን ተናግራለች።
ወጣቷ ከጅማ ዩንቨርሲቲ ሁለተኛ ድግሪዋን በባዮሜድካል እንጂነሪንግ የሰራችው ምህረት የዳይናሞ ሴንተር ፎር ቴክኖሎጅ ተቋም መስራችና ሀላፊ ስትሆን ማዕከሉ በጅማ ከተማ ሳይንስን ለታዳጊ ወጣቶች ቅርብ ለማድረግና ተመራማሪዎችንና የስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ሲሆን ይሄንንም ወደ ዎላይታ ሶዶ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማዕከል ለማስፋፋት እቅድ እንዳላት ገልፃለች።

ከአጋሮቿ ጋር ባቋቋመችው “ዳይናሞ ” የተሰኘ ስልጠና ማዕከል ለህጻናት እና ወጣቶች መሰረታዊ ቴክኖሎጂ ነክ ዕውቀትን አያስጨበጠች የምትገኘው ምህረት ከሰሞኑ ደግሞ የአይዋ ዩኒቨርሲቲ የጆን ፓፓ ጆን የስራ ዘርፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሽልማት ተሸላሚ መሆኗ በይፋ ሽልማቱን በአሜሪካ በመገኘት እንደወሰደች ከተላከልን መረጃ ለማወቅ ችለናል።
የአሜሪካ ኢምባሲ በኢትዮጵያ ባወጣው መግለጫ የወጣቷን የስራ ፈጠራ ክህሎት በማድነቅና በዘርፉ ላገኘችው ሽልማት የእንኳን ደስ አለን መግለጫ አውጥቷል።
