በዩንቨርሲቲው ድግሪ በ20 ሽህ ብር እየተሸጠ ነዉ በሚል የተሰራጨዉ መረጃ ሀሰት ነዉ ሲል አስተባበለ፡፡

በአዲስ አበባ የሚታተመዉ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ፣
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አንድ ዲግሪ በ20 ሺሕ ብር እየተሸጠ መሆኑን ባደረኩት ማጣራት አረጋግጫለሁ ሲል ዘገቦ ነበር፡፡

ጋዜጣዉ በዩኒቨርሲቲው ያሉ ሠራተኞች፤ ሰዎች በሚገዙት ዲግሪ ዙሪያ ሳይማሩ መደበኛ ተማሪ እንደሆኑ አስመስለው በ20 ሺሕ ብር ሐሰተኛ ዲግሪ እየሸጡ መሆኑን እንዳረጋገጠ ዘግቦ ነበር፡፡
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል፣ ዘገባዉ ሲሰራ በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን እንዲሰጥ ዩንቨርስቲዉ ምንም አይነት ጥያቄ እንዳልቀረበለት ተናግረዋል፡፡

ዩንቨርስቲዉ በዛሬዉ እለት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ፣የዩንቨርስቲዉ አሰራር ለእነደዚህ አይነት ችግር የሚጋብዝ ባይሆንም፣ ችግሩ መከሰት አለመከሰቱን ኮሚቴ አቋቁሞ ማጣራቱን ገልጿል፡፡

ዶክተር ፋሪስ ደሊል በማጣራት ሂደቱም ምንም አይነት ችግር እንዳልተገኘ ገልጸዉ፣ዩንቨርስቲዉ ጉዳዩን በቀጣይ ወደ ህግ እንደሚወስደዉ አስታዉቀዋል ስል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: