ባለፈው አመት አጋማሽ አካባቢ በዎላይታ ዞን የአየር ማረፊያው የሚገነባው ከዎላይታ ሶዶ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ዳሞት ሶሬ ሻምባ ቅለና እና በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋራዛ ቀበሌ ድንበር ላይ እየተገነባ የነበረው ግንባታ እንቅስቃሴ አንድ ወር ያህል መቆሙን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የየቀበሌዎቹ አስተዳዳሪዎች አረጋግጠዋል።

የሻምባ ቅለና ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጻውሎስ ናና እንዲሁም የዋራዛ ላሽ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤርምያስ እንዳረጋገጡት የአየር ማረፊያ ግንባታ እንቅስቃሴ ከቆመ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነም ተናግረዋል።

እንደ አስተዳዳሪዎች ግምት የተጨበጠ መረጃ እንደሌላቸውና ምናልባት ግንባታ በሚያከናውኑ ተቋራጮች የተፈጠረ ክፍተት ልሆን ይችላል ብለዋል።

ባለፈው አመት ሶስት ወር ገደማ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለጉብኝት ዎላይታ በመጡበት ወቅት የዚሁ አየር መንገድ ግንባታ ሂደት መመልከታቸው ይታወሳል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የዚሁ አየር መንገድ ግንባታ እንቅስቃሴ ለወራት ለምን እንደቆመ መረጃ ከሚመለከታቸው አካላት ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው ያልተሳካ ቢሆንም መረጃውን እንዳገኘን የምናደርስ ይሆናል።

ቤድሮክ በተባለ አገር በቀል ኮንስትራክሽን ድርጅት እያከናወነ የሚገኘውና ከ150 ሄክታር መሬት በላይ እየተገነባ የሚገኘው የአየር ማረፊያ ግንባታ በሶስት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎም ነበር።

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከ1950ዎቹ እስከ 1970ዎቹ ከ20 ዓመታት በላይ መንገደኞችን ሲያስተናግድ የቆየው የአውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎቱን አቋርጠው ነበር።

የዎላይታ ህዝብ በፊት የነበረው የአውሮፕላን ማረፊያ በአካባቢው እንዲገነባ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቢቆዩም፤ በ1999 የቀደሞው አውሮፕላን ማረፊያ በነበረበት ቦታ ላይ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በመገንባቱ የህዝቡ ጥያቄ ሳይመለስ እንዲቆይ መደረጉ ይታወቃል።( ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ )

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: