በዎላይታ ዞን ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የመኸር ሰብሎች ምርት የማሰባሰብ ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል።
በዞኑ በተደረገው ቅድመ ምርት ትንቢያ መሠረት ከ2012/13 መኸር ምርት 7.3 ሚለዮን ኩንታል ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዎላይታ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት መምሪያ ገለጸ።
የዎላይታ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጴጥሮስ ወልደማርያም እንደገለጹት በዞኑ በ2012/13 ምርት ዘመን በመኸር በሚለሙ ሰብሎች 73 ሺህ 1 መቶ 68 ሄክታር በማልማት 7.2 ሚለዮን ኩንታል ለማግኘት ግብ ተጥሎ ሲሰራ መቆየቱንና በቅድመ ትንቢያ መሰረት 7.3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
ምርቱ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይጎዳና አርሶ አደሩ የደከመበት ሰብል በተቋማት እገዛ እንዲሰበሰብ ከ30/02/2013 እስከ 05/30/2013 ዓ/ም የሚቆይ ምርት የማሰባሰብ ሳምንት ስለታወጀ መላው አርሶ አደርና ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ኃላፊው አሳስበዋል።
የዞንና የወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች እስከ አርሶ አደሩ ማሳ ድረስ በመሄድ በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሁሉም መዋቅሮች አስፈላጊ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።
ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ የመኸር ሰብሎች ምርትን ከብክነት ለመከላከል አርሶ አደሮች፣ ባለሙያዎችና አመራሮች በቅንጅት እንዲሰሩ አት ጴጥሮስ ጥሪ አቅርበዋል።
በዞኑ ከመኸር ሰብል ምርት ማሰብሰብ ጎን ለጎን የበጋ መስኖ ስራ ላይም ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
