የዎላይታ ሶዶ አየር ማረፊያ ግንባታ የተስተጓጎለው ደረጃውን ከፍ ለማድረግ ታልሞ እንደሆነ ግንባታውን ሲሰራ የነበረ ቤድሮክ የተባለ አገር በቀል ኮንስትራክሽን ድርጅት ገለፀ

በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትን በተደጋጋሚ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ብጠይቅም ምላሽ አልሰጠም።

በዎላይታ ዞን በሁለቱ ወረዳዎች መካከል እየተገነባ የሚገኘው አየር ማረፊያ ግንባታ ለወራት እንቅስቃሴ ማቆሙ ደረጃውን ከፍ ለማድረግ ታልሞ እንደሆነ ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው ቤድሮክ የተባለ አገር በቀል ኮንስትራክሽን ድርጅት በተላይም “ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” ገልጿል።

ባለፈው አመት አጋማሽ አካባቢ በዎላይታ ዞን
የአየር ማረፊያው የሚገነባው ከዎላይታ ሶዶ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ዳሞት ሶሬ ሻምባ ቅለና እና በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋራዛ ቀበሌ ድንበር ላይ እየተገነባ የነበረው ግንባታ እንቅስቃሴ አንድ ወር በላይ መቆሙን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የየቀበሌዎቹ አስተዳዳሪዎች ማረጋገጣቸውን ከሶስት ሳምንታት በፊት መረጃ አድርሰን ነበር።

ግንባታው የቆመበትን ምክንያት ለማግኘትና በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ የግንባታ ባለቤት የሆነውን የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ኢሜል፣ በቢሮና በግል ስልክ ላይ በተደጋጋሚ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ብጠይቅም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛነት ባለማሳየቱ ማካተት አልተቻለም።

ቢሆንም የዚሁ አየር ማረፊያ ግንባታ ለወራት እንቅስቃሴ ማቆሙ ደረጃውን ከፍ ለማድረግ ታልሞ እንደሆነ ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘውው ቤድሮክ የተባለ አገር በቀል ኮንስትራክሽን ድርጅት ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አብራርቷል።

ድርጅቱ የአየር ማረፊያ ግንባታ ሂደት በዕቅዱ መሠረት በተሻለ አፈፃፀም ላይ እያለ “ግንባታውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ” መቆሙን ገልጿል።

ባለፈው አመት ሶስት ወር ገደማ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለጉብኝት ዎላይታ በመጡበት ወቅት የዚሁ አየር መንገድ ግንባታ ሂደት መመልከታቸውን ተከትሎ የግንባታ ሂደት ከኤር ስትሪፕ ደረጃ ደረጃውን የጠበቀ ሁሉንም አይነት አውሮፕላን ማስተናገድ በሚችልበት ዘመናዊ ደረጃ እንዲገነባ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተናግረው በወሰኑት መሠረት ከአራት ጊዜ በላይ የቦታ ጥናት በከፍተኛ ባለሙያዎች መደረጉን ድርጅቱ ቢገልፅም ስለ ጉዳዩ ለህዝብ በይፋ በሚዲያ ሆነ በሌላ መንገድ አለመገለፁ ለብዙዎች ቅሬታና ጥርጣሬ ፈጥሯል።

አሁን እየተሰራ ያለው ግንባታ ሂደት ዋና ዋና ስራዎች በመጠናቀቁ ምናልባት ደረጃውን ለማሳደግ እየተጠና ባለው በአቅራቢያው የጊቤ (Uma) ሶስት ኤሌክትሪክ ኃይል ሀገራዊ ማከማቻ በመኖሩ በዞኑ ውስጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመናበብ የተሻለ ቦታ መረጣ እየተካሄደ እንደሆነ ፍንጭ ቢሰጥም ያ ስለ ግንባታው መቆም በቂ ምክንያት መሆኑን ከመናገር ተቆጥቧል።

ቤድሮክ በተባለ አገር በቀል ኮንስትራክሽን ድርጅት እያከናወነ የሚገኘውና ከ150 ሄክታር መሬት በላይ እየተገነባ የሚገኘው የአየር ማረፊያ ግንባታ በሶስት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎም ነበር።

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከ1950ዎቹ እስከ 1970ዎቹ ከ20 ዓመታት በላይ መንገደኞችን ሲያስተናግድ የቆየው የአውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎቱን አቋርጠው ነበር።

የዎላይታ ህዝብ በፊት የነበረው የአውሮፕላን ማረፊያ በአካባቢው እንዲገነባ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቢቆዩም፤ በ1999 የቀደሞው አውሮፕላን ማረፊያ በነበረበት ቦታ ላይ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በመገንባቱ የህዝቡ ጥያቄ ሳይመለስ እንዲቆይ መደረጉን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ግንባታው የቆመበትን ምክንያት ለማግኘትና በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ በኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ኢሜል፣ በቢሮና በግል ስልክ ላይ በተደጋጋሚ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ብጠይቅም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛነት ባለማሳየቱ በዚሁ ዜና ማካተት ባይቻልም ከድርጅቱ ምላሽ እንዳገኘን መረጃውን እንደምናደርስ እናሳውቃለን። በዎላይ ታይምስ ሚዲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: