በዎላይታ ዞን በመንግስት ተቋም ቢሮ ገብቶ  ሰውን የመግደል ሙከራ ያደረገው ግለሰብ በወንጀል ተከሶ በ11 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

በዎላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት በዋለው ችሎት በሁለት ተከሳሾች ላይ ከባድና ቀላል የወንጀል ፍርድ ወሳኔ አስተላልፏል።

በከሳሽ በዎላይታ ዞን ከፍተኛ ዐቃቤ ህግ የተከሰሱ፦
1ኛ .ዶክተር ገለታ ጴጥሮስ ዴአ
2ኛ. እና
3ኛ.ብርሀኑ እሸቱ ዘለቀ ላይ በተከሰሱበት ወንጀል ክስ መዝገብ በመመርመር ችሎቱ ብይን ተሰጥቷል።

በኢፌዲሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 27 (1) እና 539 (1) (ሀ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ 1ኛ ተከሳሽ ካልተያዘው ቢኒያም ሶርሳ ጋር በመሆን አስቀድሞ ሰውን ለመግደል ባለው ሀሳብ ተዘጋጅቶ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ በቀን 9/12/2014 ዓ/ም ዕለተ ሰኞ ከቀኑ በግምት 6:30 ሰዓት አከባቢ በሶዶ ከተማ አስተዳደር ልዩ ቦታ ዎላይታ ዞን ጤና መምሪያ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል።

አንድኛ ተከሳሽ በግል ተበዳዩ ላይ በበሌ ከተማ ያስከፈትኩትን መልካም መድሀኒት መደብር አሳሽጎብኛል በሚል ምክንያት ቂም ይዞ በአካልም ሆነ በፌስቡክ ገጹ ስሜታዊ ሆኖ የጥለቻ ንግግር በማሰራጨትና በአካል ሲያስፈራራ ከቆየ በኋላ ገዳይ መሳሪያ (ሽጉጥ) ይዞ ቢሮ ድረስ በመግባት ግል ተበዳይ አሳምነው አይዛ የተባለውን የዎላይታ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊን በራሱ ቢሮ ውስጥ ግንባሩ ላይ ሁለት ጊዜ ሲተኩስ ግል ተበዳዩ ተደብቆ ከሞት መትረፍ መቻሉን ከሰውና እጅ ከፈንጂ ከተያዘው ጦር መሣሪያ(ሽጉጥ) ማስረጃ ለማወቅ መቻሉን በችሎት ተገልጿል።

አንደኛ ተከሳሹ ከነ ሽጉጡ ከግቢ ሳይወጣ የተያዘ ስለሆነ በፈጸመው ከባድ የሰው ግድያ ሙከራ ወንጀል ከመከሰሱ በተጨማሪ የኢፌዲሪ ጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 ዓ/ም አንቀጽ 22 (2)፣ ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ከላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በፈጸመው በህግ የፀና ፈቃድ ሳይኖረው ጦር መሳሪያ (ሽጉጥ) በመያዝና በግድያ ሙከራ ወንጀል ተከሷል፡፡

እንድሁም በሶስተኛ ኪሱ ላይ እንደተመለከትነዉ የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4፣ አንቀጽ 7 (2) ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ በግል ተበዳይ ላይ ጥላቻና ሐሰተኛ መሬጃ በስሙ በተከፈተው ፌስቡክ ገጹ ላይ በማስተላለፍ በግል ተበዳዩ ላይ ሲያሰራጭበት ቆይቷል።

2ኛ ተከሳሹ በሀሰተኛ ፌስቡክ ገጹ 1ኛ ተከሳሹን በማበረታታት ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን በማለት ወንጀል ውስጥ እንዲገባ አድርጓል።

2ኛ ተከሳሽ 1ኛውን ተከሳሽ የወንጀል ድርጊቱን በግል ተበዳዩ ላይ እንዲፈጽም አነሳስቷል።

3ኛ ተከሳሽ ግል ተበዳዩ መሞት ነበረበት በማለት ድምጹ አውጥቶ ለሌሎች በመናገር ጥላቻውን የገለጸ ስለሆነ ተከሳሾች በፈጸሙት ጥላቻ ንግግር በማድረግና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ወንጀል ተከሰዋል፡፡

በከሳሽ በዎላይታ ዞን ከፍተኛ ዐቃቤ ህግ
የተከሰሱ 1ኛ ዶክተር ገለታ ጴጥሮስ ዴአ በፈጸመው ከባድ ሰውን በመግደል ሙከራና በጥላቻ ንግግር ተከሶ በ11 ዓመት ጽኑ እስራት እንድቀጣ ተወስኗል።

2ኛ ተከሳሽ በቀላል ወንጀል ተከሶ የ4 ወር ፍርድ የተበየነ ስሆን 3ኛ ተከሳሽ ብርሀኑ እሸቱ ዘለቀ በወንጀል ከተከሰሰው ክስ ከወንጀል ክሱ በነጻ ተሰናብቷል ስል የዞኑ ፍትሕ መምሪያ ልዩ ልዩ ወንጀል ጉ/ ሥ/ሂደት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *