በደቡብ ክልል በተለይም በዎላይታ ዞን ከተለያዩ አለምአቀፍ ተቋማት ለጤና ስራ የሚበጀተው ገንዘብ ላልተፈለገ አላማ እንደሚውል ተገለፀ።

በአሁኑ ወቅት የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ትኩረት ባለመሰጠቱ በዞኑ ባሉ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች መስረታዊ የሚባሉ የህክምና ቁሳቁስ ባለመኖሩ የብዙ እናቶችና ህፃናት ህይወት ማዳን እየተቻለ እየሞቱ መሆኑንም የጤና ባለሙያዎች ገልጿል።

ለህብረተሰቡ ጤና አጠባበቅ ስባል በመቶ ሚሊዮኖች ከለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች የሚመደበው ገንዘብ ለፓለቲካ ስራዎችና ለአመራር በአበል መልክ ስለምከፋፈል በአከባቢው የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ስራ አስቸጋሪ እያደረገ መሆኑንም በዎላይታ ዞን በተለያዩ መንግስት ሆስፒታሎች የሚሰሩ ዶክተሮች ያደረሱት መረጃ ያመለክታል።

እንደ ዶክተሮቹ እና ሌሎች የጤና ባለሙያዎች ገለፃ በአሁኑ ወቅት በዎላይታ ዞን ባሉ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች መስረታዊ የሚባሉ የህክምና ቁሳቁስ ባለመኖሩ የብዙ እናቶችና ህፃናት ህይወት ማዳን እየተቻለ እየሞቱ መሆኑን ለ”ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” ተናግረዋል።

ለአብነትም በዞኑ በቦሎሶና ቢጣና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች የእናቶችንና የህፃናት ህይወት ለማዳን ቀላል የሚባሉ የህክምና ቁሳቁስ እንኳን ባለመኖሩ ማትረፍ እየተቻለ ሞት እየተከሰተ መሆኑንም ስማቸው ከተገለፀ የተለያዩ ጫናዎች ይደርስብናል ያሉ ዶክተሮች አክለው ገልጸዋል።

በተጨማርም እንደ ጤና ባለሙያዎች ገለፃ በዞኑ በአብዛኛው ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ላይ የትርፍ ጊዜ ክፍያ ለረጅም ጊዜ እንደማይከፈልና ለህብረተሰቡ ጤና አጠባበቅ ስባል ከተለያዩ አለምአቀፍ ተቆማት ድርጅቶች በርካታ ሚሊዮን ብሮች የሚመደበው ገንዘብ ለፓለቲካ ስራዎችና ለአመራር ስብሰባ ምክንያት በማድረግ በአበል መልክ ስለሚውል በአከባቢው የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ስራ አስቸጋሪ እያደረገ መሆኑንም በዞኑ በተለያዩ መንግስት ሆስፒታሎች የሚሰሩ ዶክተሮች “ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” ያደረሱት መረጃ ያመለክታል።

ዎላይታ ዞን ዉስጥ ያሉ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች የድንገተኛ ኦፕራስዮን አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉና ሆስፕታሎቹ ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ የተመረቁና ደረጃቸዉን የምመጥን አገልግሎት የምሰጡበት የምርመራ መሳሪያ፣ መድኃኒት እንዲሁም ባለሙያዎች የለላቸዉን መሆኑ ለህዝቡ ልሰጠዉ የሚገባዉ አገልግሎት እንዳይሰጥ እንዳደረገ ተናግረዋል።

ለዚህም ራሳቸዉ ሆስፒታሎች ወደ ዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ኮምፕረንሲቪ ሆስፒታል በላኩበት በሪፈራል ወረቀት ላይ የምንሰራበት ኦፕራስዮን የለንም(No Functional OR) በማለት የጻፉበት አንዱ ማስረጃ ነዉ ስሉም ባለሙያዎቹ ሁኔታዎች አብራርተዋል።

የህክምና ባለሙያዎቹ በጤና ተቋማት ያለውን ተጨባጭ ችግር ማውራት፣ የትርፍ ጊዜ ክፍያ መጠየቅ እንዲሁም የትኛውም አይነት የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት በየትኛውም መንገድ ማጋለጥ ከሰራ የሚያስባርር እንዲሁም የተለያዩ ጫናዎች እንዲደርስባቸው የሚያደርግ ነው” በማለት ገልፀው “ይሄንንም ጥልቅ የመልካም አስተዳደር ችግር በግልጽ ለህዝብ ይፋ ለማድረግ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በነፃነት የመስራት ዕድል ማግኘቱ በራሱ ትልቅ ድልና ነገሮቹ እንዲስተካከሉ በር ከፋች ይሆናል” ስሉም መረጃውን ያደረሱ ባለሙያዎች በደስታ ሁኔታውን አስረድተዋል።

በባለሙያዎች የተነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በተመለከተ ማብራሪያና ምላሽ እንዲሰጡ የዎላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ግልና በቢሮ ስልክ በተደጋጋሚ ብንደወልም ምላሽ አላገኘንም፣ በተጨማሪም ወደ ደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊውን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ቢሆንም ምላሽ ካገኘን መረጃውን እንደሚናደርስ እናሳውቃለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *