እያንዳዳቸው የደቡብ ክልል ምክርቤት አባላት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ተከፋፍለው መውሰዳቸው ተገለፀ

የሲዳማ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አዲስ ክልል አደረጃጀት ተክትሎ ለብቻው የቀረው የቀድሞ ደቡብ ክልል ምክርቤት አባላት እያንዳንዳቸው ምክንያቱ ያልታወቀ ገንዘብ በስማቸው ወጪ ተደርጎ እንደተሰጣቸው በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በከፍተኛ ህሳብ ባለሙያነት የሚሰራ “ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” አስረድተዋል።

እንደ ባለሙያው ገለፃ ለእያንዳንዳቸው የምክርቤት አባላት ግማሽ ሚሊዮን ብር የተሰጠ ሲሆን ለቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች በስማቸው አንድ አንድ ሚሊዮን ብር ከመንግሥት ካዝና ወጪ ተደርጎ መሰጠቱን ስሙን ለድህነቱ ያልገለፀው ከፍተኛ ፍይናንስ ባለሙያ አብራርተዋል።

የተከፋፈሉት ገንዘብ ለክልሉ መንግስት ከፌደራል በድጎማ ስምና ለአገደጋ ጊዜ እርዳታ ስም ከመጣ በጀት መሆኑን ጠቅሰው በየጊዜው ገንዘብ ያለህጋዊ አሰራር ወጪ እንደሚሆን አስረድተዋል።

በተለይም በክልሉ ለሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ከህዝብ ከመንግሥት መዋቅሮች በጥሬ ገንዘብና በአይነት የተሰበሰበው ወደ ማዕከል ሙሉበሙሉ ሳይደርስ በኮሚቴ የተዋቀሩ ግለሰቦችና አመራሮች ክስ በሚሊዮን የሚቆጠር ስገባ እንደነበር ገልጸዋል።

በጦርነቱ ወቅት ህዝብ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ከየቤቱ፣ መንግስት ሰራተኞች ከደሞዛቸው ሳይወዱ በግድ የሰጡትን ገንዘብ በተጨባጭ ለግል ጥቅም በተደራጀ መንገድ ያዋሉ ከወረዳ፣ ከዞንና ክልል ድረስ በከፍተኛ አመራሮች መኖሩን አረጋግጠዋል።

ለአብነትም በዎላይታ ዞን ከደሞት ፑላሳ ወደ መካላከያ ሰራዊት ድጋፍ ተብሎ በሶ በማስመሰል የከብት መኖ (ፉሩሽካ) ከፌደራል ወደሁዋላ ተመልሶ በክልሉ ፀረሙስና ኮሚሽን ብገባም፣ በተጨማሪም ከህዝብ የተሰበሰበውን ገንዘብ ለራሳቸው ያዋሉ አመራሮች ጭምር በኦዲት ተረጋግጦ ቢቀርብም በጫና ወሳኔ እንዳይሰጥበት ተደርጓል ስል ባለሙያው ያብራራል።

ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ “ክልሉ ይፈርሳል” በሚል ለመናገር በሚከብድ ሁኔታ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ እንኳን በግዜ ሳይሰጥ በሚቸገሩበት ክልል በየመስሪያ ቤቱ ህገወጥ አሰራር ተዘርግቶ በተለይም ከሰሜን ጦርነት ወቅት ጀምሮ ዝርፊያ መጧጧፉንም በቁጭት ተናግረዋል።

አሁን ባለው ሁኔታ በክልሉ የፋይናንስ ስራአትን እየመራ ያለው ህጋዊ አሰራር ሳይሆን አመራር በስልክ ባዘዘው መንገድ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ካለ በየመስሪያ ቤት ገብቶ የኦዲት ስራ ሰርቶ አለአግባብ በተደራጀ መንገድ የተዘራውን የህዝብና የመንግስት ሀብት ብያስመለስ ይሻላል ስሉም ባለሙያው ተማፅነዋል።

በየወቅቱ የሚስተዋሉ መሰል ችግሮችን ለማጋለጥ የተቋቋሙ መስሪያ ቤቶቹም ከጥቅመኞች ጋር ተባባሪ ስለሆኑ ለማን አቤቱታ እንደሚናቀርብና ብናቀርብ እንኳን የሚደርሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑ ለእውነት የሚሟገቱ ሰዎች ጭምር ዝምታ እንዲመርጡ አድርጓል ስል ለ”ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” ከተለያዩ ሰነዶች ጋር መረጃ ሰጥተዋል።

የሲዳማ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አዲስ ክልል አደረጃጀት ተክትሎ ለብቻው የቀረው የቀድሞ ደቡብ ክልል ምክርቤት አባላት እያንዳንዳቸው ምክንያቱ ያልታወቀ ገንዘብ በስማቸው ወጪ ተደርጎ የተሰጣቸው በክልሉ የተለያዩ ዞኖች በክልል ለመደራጀት ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አድርገው በክላስተር እንዲደራጁ የወሰኑ መሆኑም ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: