ሰበር ዜና

ኢህገመንግስታዊ ክላስተር የሚባል አደረጃጀት በአስቸኳይ ቆሞ ዎላይታ ብቻዬን ክልል ልሁን የሚል አማራጭ እንዲቀርብ በአፅንኦት ተጠየቀ።

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎህዴግ) ማምሻውን ባወጣው ጠንከር ያለ መግለጫ ኢህገመንግስታዊ ክላስተር የሚባል አደረጃጀት በመፍጠር የዎላይታ ህዝብ ባለቤት ያላደረገ አካሄድ በአስቸኳይ ቆሞ ብቻዬን ክልል ልሁን የሚል አማራጭ እንድቀርብ ፓርቲያችን አበክሮ ይጠይቃል ስል ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በላከው መረጃ አመላክቷል።

የግንባሩ ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የዎላይታ ሕዝብ ሀለንተናዊ ለውጥ ማለትም ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፓለቲካዊ መብቱን እንደጎናጸፍ ለበርካታ አመታት ሕዝቡን በማስተባበር ሰላማዊ ትግል እያደረገ መቆየቱንና እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎህዴግ) በተለይ ባለፉት አራት አመታት ወድህ በሕዝባችን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን እጅግ የከፋ መዋቅራዊ ጫና አሽቀንጥሮ ለመጣልና ሕዝቡ ሕገመንግሥታዊ ራሱን በራሱ የማስተዳር መብቱን እንድጎናጸፍ ጠንካራ ሰላማዊ ትግል ማድረጉና እያደረገም መሁኑ እሙን ነው።

ይሁን እንጅ ሕዝቡ ያነሳውን የመብት ጥያቄ ኢ-ሕገመንግሥታዊ በሆነ አካሄድ የራሱን መብት እንዳይጎናጸፍ ተከልክሎ ሕዝቡ በብሔሩ ምክር ቤት ከቀበሌ ጀምሮ ራሴን በራሴ አስተዳድራለሁ ብለው ወስኖ ለክልል ም/ቤትም: ለፌድረሽን አቤቱታ አቅርቦ ምላሽ እየተጠባበቀ በነበረበት ወቅት የዞን ም/ቤት የምርጫ ዘመኑን ባጠናቀቁትና ጊዜ ባለፈቸባቸው አባላት የሕዝቡን ሕገመንግሥታዊ ውሳኔ በሀይል ሽሮ በክላስተር እንደራጃለን በማለት ሕገወጥ ውሳኔ ማስተላለፉ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ይህንን ተከትለው ፓርቲያችን ዎህዴግ ይህንን ኢ-ህገመንግስታዊ ተግባር በአጽንኦት ከመቃወሙ ባሻገር በየደረጃው በጽሑፉ ማሰማቱ ይታወቃል።

ሆኖም ግን ይህ ኢ-ህገመንግሥታዊ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሎ የዎላይታ ሕዝብ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለበት ሕገመንግስታዊ የዎላይታ ብሔራዊ ክልል እመሰረታለሁ የሚል አማራጭ ተፍቆ ሌላው ደፍጣጭ ሕዝበውሳኔ ለማድረግ ደፋ ቀና መባሉ ቀጥሎበታል። ስለሆነም የዎላይታ ሕዝብ ደሞክራሲያዊ ግንባር ዎህዴግ በተደጋጋሚ ተቃውሞን አሰምቷል። እያሰማም ይገኛል።ከዚህም ባሻገር የሕዝበ ውሳነውን ሕደቱንም ይሆን እንድሁም የሕዝበ ውሳኔን በተመለከተ ያሉትን ተግባራትን በአጽንኦት የሚቃወምና ዕውቅና የማይሰጥ መሆኑን በአጽንኦት እየገለጠ ባለ ሶስት ነጥብ አቋም መግለጫ አውጥቷል።

1.የህዝቡን ህገመንግስታዊ መብት ደፍጥጦ በኢህገመንግስታዊ አካሄድ የሚደረግ ህዝበውሳኔ ፓርቲያችን አጥብቆ ያወግዛል።

  1. በጥር 29, 2015 ዓ.ም መጨረሻ ልደረግ ቀን የተቆረጠለት የአንድ ፓርቲ ውሳኔ ተሽሮ በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀጽ 47/3 መሠረት የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በፈለጉ ጊዜ የራሳቸውን ክልል ይመሰርታሉ የሚለውን ህገመንግስታዊ ድንጋጌ በመቃረን ኢህገመንግስታዊ ክላስተር የሚባል አደረጃጀት በመፍጠር የዎላይታ ህዝብ ባለቤት ያላደረገ አካሄድ በአስቸኳይ ቆሞ ብቻዬን ክልል ልሁን የሚል አማራጭ እንድቀርብ ፓርቲያችን አበክሮ ይጠይቃል።
  2. የህዝቡን የመልማትና ፍትሐዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ያላረጋገጠ የአንድ ፓርቲ ጠቅላይ ገዥነት አካሄድ ቆሞ ሁሉን ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ሥራ አጥነት የሚቀንስ የኢኮኖሚ ትግበራ በዎላይታ እንዲከናወን ዎህደግ ያሳስባል።

የዎላይታ ሕዝቦ ዴሞክራስያዊ ግምባር(ዎህዴግ) ሥራ አሰፈጻሚ

ጥር 2/2015 ዓም
ዎላይታ ሶዶ
ኢትዮጵያ

የዩቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/@wolaitatimes

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: