
በዎላይታ ዞን ከስምንት ሺህ በላይ ኩንታል ስኳር በማጭበርበር በህገወጥ መንገድ በአመራሮችና ግለሰቦች እጅ መግባቱ ተገለጿል ።



በዚሁ የማጭበርበርና የሙስና ቅሌት ወንጀል ውስጥ በቀጥታ የተሳተፈችው የቀድሞ የዎላይታ ዞን ሕብረት ሥራ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ሣሙኤል በጥፋቷ ተገምግማ ከኃላፊነት ቦታዋ ተነስታ በዎላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ም/ኃላፊና የገጠር መሬት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ እንዲትሆን መሾሟ አነጋጋሪ መሆኑም ተነግሯል።
በተጨማሪም ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው የዎላይታ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ወርሴሶ (አሁንም በስልጣን ላይ የሚገኝ) እና የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የሕብረት ሥራ ጽ/ቤት ኃላፊና የዘርፉ ባለሙያዎች እንዲሁም የዩኒዬኑ አመራሮች ላይ ሰፊ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ የተጠናቀቀ ሲሆን ክስ ለመመስረት ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።
ከ8000 ኩ/ል በላይ ስኳር በሕግ ወጥ መንገድ በግለሰቦች መበላቱን ስሙን ለደህንነቱ ስል ያልገለፀ የዞኑ ህብረት ስራ ዩኒዮ ከፍተኛ ባለሙያ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በመረጃ አስደግፎ ማድረሱን መዘገባችን ይታወሳል።
ስኳር በየ45 ቀን ለህብረተሰቡ ከመንግሥት በድጎማ የሚቀርብ ስሆን በ2014 ዓ.ም በተደጋጋሚ አልመጣም፣ እጥረት አለ፣ መንገዱ በጸጥታ ምክንያት ዝግ ነው እየተባለ በርካታ ዙር እንዳልቀረበ ህዝቡ ያዉቃል፤ ቅሬታም እያቀረበ ቆይቷል ስል መረጃው ያብራራል።
ከዚህ መነሻ በህብረተሰቡ ላይ ጉዳት ያደረሱ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ ለፀረ-ሙስና መስሪያ ቤት መረጃ በመድረሱ የማጣራት ሥራ እየተሰራ ቢቆይም ፀረሙስና እንቅስቃሴ ከጀመረ በኋላ መረጃ እንዳይወጣ በተለያዩ አካላት ለመዝጋት ሙከራ ተደርጓል።
በመጨረሻም ከፍተኛ ትግል ተካሂዶ የተባለው 8000 ኩንታል በላይ ስኳር በግለሰቦች ወጪ የሆነ ቢሆንም ለኅብረተሰቡ እንዳልደረሰ ስኳር ኮርፖሬሽን ማረጋገጫ ደብዳቤ ለፀረ ሙስና ኮሚሽን መስጠቱንም ባለሙያው አስረድቷል።
በዚህ የማጭበርበርና የሙስና ወንጀል ውስጥ የተሳተፉ አካላት ላይ የክልሉ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የዎላይታ ዞን ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዩኒት እና የዎላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ሥራውን በማጠናቀቅ ክስ እንዲጀመር የማድረግ ሥራ እየተጠናቀቀ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ከመንግስት ጋር በገባው ውል መሠረት የድጎማ ስኳርን በፍትሃዊነት ለተጠቃሚው ሕዝብ ማሰራጨት ባለመቻሉ ውሉ እንዲሰረዝና ሌላ ማህበር የድጎማ ስኳር እንዲያሰራጭ እንዲደረግ የዎላይታ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ለደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በቀን 5/5/2015 ዓ.ም ደብዳቤ በመጻፉ ምክንያት ዩንዬኑ ስኳር እንዳያሰራጭም ታግዷል።
በዚህ የማጭበርበርና የሙስና ቅሌት ወንጀል ውስጥ በቀጥታ የተሳተፈችው የቀድሞ የዎላይታ ዞን ሕብረት ሥራ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ሣሙኤል በጥፋቷ ተገምግማ ከኃላፊነት ቦታዋ ተነስታ በዎላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ም/ኃላፊና የገጠር መሬት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ እንዲትሆን የተደረገ ቢሆንም በሙስና ወንጀል በቀጥታ በመሳተፏ ምርመራ እየተካሄደባት ይገኛል።
በጉዳዩ ዙሪያ ለWT ሚዲያ የደረሱ በርካታ ተጨባጭ ሰነዶች በምርመራ ሂደት ላይ በመሆኑ ለጊዜው ይፋ ባናደርግም ወደፊት ተጨማሪ መረጃ ታክሎበት የሚናደርስ ይሆናል።