

ከ421 አባወራዎች መካከል ለ20 አርሶአደሮች ብቻ ካሳ ቢከፍልም ከተከፈለው ውስጥ 14 አባወራዎች በአከባቢው የሌሉና የት አከባቢ ነዋሪዎች እንደሆኑ የማይታወቁ መሆኑን የአከባቢው አርሶአደሮች አጋልጧል።
በዎላይታ ዞን የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት ምክንያት 421 አባወራዎች ከአከባቢው እንድነሱ የታዘዙ ሲሆን ለቤታቸውና ለንብረታቸው ምትክ ካሳ ከ10 እስከ 14 ሚልዮን ብር ድረስ ተገምቶ እንደሚከፍልላቸው ተነግሮ እንደነበር WT ሚዲያ መረጃ ማድረሱ ይታወቃል።
ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት ከ421 አባወራዎች መካከል 20 አርሶአደሮች ብቻ ካሳ እንደተከፈለ ለWT Media የደረሰው መረጃ ያመለክታል። ሌሎች ግን “የግምት ሰነድ ማረጋገጫ ካላመጣችሁ አይከፈልም ተብለናል” ደግሞ ከእነሱ ውስጥ 14 አባወራዎች በአከባቢው የሌሉ እንዲሁም የት አከባቢ ነዋሪዎች እንደሆኑም መረጃ የሌላቸው ሲሆኑ በስማቸው 10-14 ሚልዮን ብር ድረስ የካሳ ግምት ሰነድ የተዘጋጀላቸው እንደሆኑ ከፈዴራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን መጣን የሚሉ አካላት ከአባባቢው አርሶአደሮች ጉዳዩን አጣሪቶ ሄዶ በዛው መቅረቱ ቅሬታ እየፈጠረ መሆኑን የአከባቢው አርሶአደሮች ገልጿል።


አሁንም ከቀሪ አርሶአደሮች መካከል “የአራቱ አርሶአደሮች ሰነድ ተገኝተዋል ካሉ በኃላ በመሃል ከተመደበው ካሣ ገንዘብ ውስጥ 8 ሚልዮን ብር ብቻ ይደርሳቸዋል ካልሆነ ግን ግምቱን አሳንሰን እንከፍላለን አሉ፤ ለምን ስንል ገንዘቡ እዛ ፈዴራል ተቆርጦ ነው የሚመጣው ከተሠማማችሁ ግን በተባለው ልክ የተገመተውን ወይም በግምት ሰነድ ላይ ካለው ሙሉን ገንዘብ ፈርማችሁ 8 ሚሊዮን ብር ትወስዳችሁ፤ ቀሪውን አትጠይቁን” ብለው በሚስጥር ማነጋገራቸውንም አርሶአደሮቹ ገልጿል።
ይህንን ለምን ያሉ አርሶአደሮች በሙሉ ቋሚ ንብረታቸውን አጥተው ያለ ካሳ ተፈናቅለው እንደሚገኙ የተገኘው ተጨማሪ መረጃ ያስረዳል።
“የግምት ሰነድ ዋናውን አታለው ከወሰዱባቸው አርሶአደሮች መካከል አንዱ የሰነድ ማረጋገጫ ከሌለ የሚከፈል ገንዘብ የለህም” ተብሎ በመነገሩ ከጭንቀት የተነሳ ተሰቅሎ ህይወት ማለፉንም ከአከባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
አርሶአደሮቹ ለፕሮጀክቱ መጀመር መሬታቸውን ያለምንም ቅድመ ክፍያ በፈቃደኝነት ቢለቁም ለሁለት ዓመት ካሳ ስላልተከፈላቸው ችግር ላይ በመሆናቸው ማዘናቸውን ተናግረው፤ ሥራ ቢጀምር ከልማቱ ተጠቃሚ ስለሚሆኑና የመሬታቸው ካሳ ቶሎ እንዲከፍልና በዎላይታ ዞን ማንነታቸው በማይታወቁ አርሶአደሮች ስም በአመራሮች የተጭበረበረው ከ200 ሚሊዮን ገንዘብ ጉዳይ ተጠርቶ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀው ጠይቋል።
የፕሮጀክቱ አማካሪ መሀንዲስ ፍፁም አሰፋም በበኩላቸው ፕሮጀክቱ የሚያርፍበት መሬት ካሳ ስላልተከፈለ ሥራ ተቋራጩ በሙሉ አቅሙ እየሠራ ባለመሆኑ በእቅዱ መሠረት አሁን መድረስ ከነበረበት 36 በመቶ የሥራ ክንውን 9 በመቶ ብቻ ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡


የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት በ2.4 ቢሊየን ብር፣ 3 ሺህ 371 ሄ/ር መሬት የሚያለማና 12 ሺህ ባላይ አባወረዎችን ተጠቃሚ የሚደርገቸው ተብሎ ከሁለት ዓመት በፊት መሠረት ድንጋይ መቀመጡ ይታወቃል። በዎላይታ ታይምስ ሚዲያ