ሰሞኑን የጎንደር በዓታ ለማርያም ጥንታዊ ገዳም አበምኔት የሆኑት ሊቅ  አባ ኃ/ገብርኤል ንጋቱ ባሉበት ከተማ ጎንደር ከተማ “ለፓለቲካ አላማ መጠቀሚያ ለማድረግ በጥይት ተደብድበዉ ህይዎታቸው ማለፉን” መዘገባችን ይታወሳል።

ከትናንት ወዲያ በዋልዲባ ገዳም ግብዓተ መሬታቸው ተፈፅሟል። ዛሬ ደግሞ በዎላይታ ባህል የለቅሶ ስርዓት መከናወኑ ተገልጿል።

አባት ቆሞስ አባ ወልደገብርኤል የተወለዱት በዎላይታ ዳሞት ጋሌ ቦድቲ አካባቢ ሲሆን ያደጉት ፋንጎ ቦሎሶ በተባለ አካባቢ ነበር:: ከልጅነታቸው ጀምሮ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በተለያዩ ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን ለረጅም ጊዜ ትናንት ህይወታቸው እስካለፈበት ዋልድባ ገዳም እያገለገሉ እንደነበሩ ከግል ማህደራቸው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ቆሞስ አባ ወልደገብርኤል የፊታችን ግንቦት ርክበ ካህናት ዕጩ ጳጳስ እንደነበሩና እጂግ የተረጋጉ በጥበብ የተሞሉ አባት ስለመሆናቸው ከቤተክርስቲያን ሰዎች ተረድተናል።

በርካቶች “ቤተክርስቲያኗም የአባታችን የግፍ ግድያ በተመለከተ ግልጽ ማብራሪያ እንድትሰጥ በአክብሮት እንጠይቃለን” በሚል ድምፅ እያሰሙ ይገኛሉ። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *