

“የልዩ ኃይል መፍረስ ውሳኔ በድንገት የመጣ ነው” በሚል በተፈጠረው አለመግባባት በደቡብ ክልል 11 ከፍተኛ መኮንኖች ጨምረው የልዩ ኃይል አባላት ህይወት አለፈ።
በክልሉ እስካሁን በተፈጠረው ከፍተኛ ተቋውሞ እና ግጭት ወደ ተግባር አለመገባቱና በመካከላቸው ውጥረት መንገሱ ተገልጿል።
በደቡብ ክልል የልዩ ኃይል መበተን ያልታቀደና የሰራዊቱን ማህበራዊ ህይወት ከግንዛቤ ያላስገባ ነው በሚል በተፈጠረው ከፍተኛ አለመግባባት በቀን 6/08/2015 ዓ.ም ሶስት ከፍተኛ መኮንኖች ጨምረው ስምንት የልዩ ኃይል አባላት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከአስር በላይ የልዩ አባላት ላይ ጉዳት መድረሱን አንድ ለደህንነቱ ስሙን መጥቀስ ያልፈለገ የልዩ አባልና አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያደረሰው መረጃ ያመለክታል።
“የልዩ ኃይል መበተን ያልታቀደና የሰራዊቱን ማህበራዊ ህይወት ከግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ ነው፥ የልዩ ኃይል መፍረስ ውሳኔው በድንገት የመጣ ትዕዛዝ ነው፣ ልዩ ኃይሉን ለአመታት ከመሰረተባቸው ማህበራዊ ህይወት አከባቢ በድንገትና በግዳጅ ወደ መከላከያ ሰራዊት ተቀላቀሉ መባሉ” ከከፍተኛ መኮንኖች ጀምሮ ልዩ ኃይል አባላት ድረስ ተቋውሞ በማሰማታቸው በተፈጠረው አለመግባባት መሆኑንም ኮማንደሩ ለWT ሚዲያ አስረድተዋል።



የልዩ ኃይል መበተን ያልታቀደና የሰራዊቱን ማህበራዊ ህይወት ከግንዛቤ ያላስገባ ነው በሚል በተፈጠረው ከፍተኛ አለመግባባት ሶስት ከፍተኛ መኮንኖች ጨምረው ስምንት የልዩ ኃይል አባላት ህይወታቸው ያለፈው ከአስር በላይ የልዩ አባላት ላይ ጉዳት የደረሰባቸው በደቡብ ኦሞ ጅንካ አከባቢ በግዳጅ ቀጠና የሚኖሩትን በድንገት ወደ መከላከያ ሰራዊት ትገባላችሁ የሚል ምዝገባ ለመጀመር እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተከትሎ መሆኑንም የመረጃ ምንጫችን አስረድተዋል።
በዚህም ምክንያት በክልሉ በሁሉም ቦታ እስካሁን የልዩ ኃይል አደራጃጀቱ በተፈጠረው ከፍተኛ ተቋውሞ እና ግጭት ወደ ተግባር አለመገባቱና በመካከላቸው ውጥረት መንገሱ ተገልጿል።
